Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 29:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ለላባም ሁለት ሴቶች ልጆች ነበሩት፥ የታላቂቱ ስም ልያ የታናሺቱ ስም ራሔል ነበረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ላባ ሁለት ሴቶች ልጆች ነበሩት፤ የታላቂቱ ስም ልያ የታናሺቱ ራሔል ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ላባ ሁለት ሴቶች ልጆች ነበሩት፤ ታላቂቱ ልያ፤ ታናሽቱ ራሔል ይባሉ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ለላ​ባም ሁለት ሴቶች ልጆች ነበ​ሩት፤ የታ​ላ​ቂቱ ስም ልያ የታ​ና​ሺ​ቱም ስም ራሔል ነበረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ለላባም ሁለት ሴቶች ልጆች ነበሩት፤ የታላቂቱ ስም ልያ የታናሺቱ ስም ራሔል ነበረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 29:16
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በከተማይቱ በር አደባባይም የነበሩ ሽማግሌዎችና ሌሎችም ሰዎች ሁሉ፦ “እኛ ምስክሮች ነን፥ ጌታ ይህችን ወደ ቤትህ የምትገባውን ሴት የእስራኤልን ቤት እንደ ሠሩ እንደ ሁለቱ፥ እንደ ራሔልና እንደ ልያ ያድርጋት፥ አንተም በኤፍራታ ባለ ጠጋ ሁን፥ ስምህም በቤተልሔም ይጠራ።


አብርሃምና ሚስቱ ሣራ ከዚያ ተቀበሩ፥ ይስሐቅና ሚስቱ ርብቃ ከዚያ ተቀበሩ፥ ከዚያም እኔ ልያን ቀበርኋት፥


ልያ በፓዳን-ኣሪም በሶርያ ለያዕቆብ የወለደቻቸው ልጆችና፥ ሴቲቱ ልጇ ዲና እነዚህ ናቸው፥ ወንዶችም ሴቶችም ልጆችዋ ሁሉ ሠላሳ ሦስት ናቸው።


የልያ ልጆች፥ የያዕቆብ በኩር ልጅ ሮቤል፥ ስምዖን፥ ሌዊ፥ ይሁዳ፥ ይሳኮር፥ ዛብሎን፥


ያዕቆብም ላከና ራሔልንና ልያን በጎቹ ወደ ነበሩበት መስክ ጠራቸው፥


ልያም ደግማ ፀነሰች፥ ስድስተኛ ወንድ ልጅንም ለያዕቆብ ወለደች።


ልያም ዓይነ ልም ነበረች፥ ራሔል ግን መልከ መልካም ነበረች ፊትዋም ውብ ነበረ።


ሴት አገልጋዮቹንና ልጆቻቸውንም ከፊት አደረገ፥ ልያንና ልጆችዋንም አስከተለ፥ ከዚያም ራሔልንና ዮሴፍን ከሁሉ በኋላ አደረገ።


ላባም ያዕቆብን፦ “ወንድሜ ስለሆንህ በከንቱ ታገለግለኛለህን? ደመወዝህ ምንድነው? ንገረኝ” አለው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች