Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 29:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ያዕቆብም ተነሥቶ ወደ ምሥራቅ ሰዎች አገር ሄደ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ያዕቆብም ጕዞውን ቀጠለ፤ የምሥራቅም ሰዎች ወደሚኖሩበት ምድር ደረሰ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ያዕቆብ ጒዞውን ቀጥሎ በስተምሥራቅ ወዳለው አገር ደረሰ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ያዕ​ቆ​ብም በማ​ለዳ ተነ​ሥቶ የያ​ዕ​ቆ​ብና የዔ​ሳው እናት የር​ብቃ ወን​ድም የሶ​ርያ ሰው የባ​ቱ​ኤል ልጅ ወደ​ሚ​ሆን ወደ ላባ ሄደ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ያዕቆብም ተነሥቶ ወደ ምሥራቅ ሰዎች አገር ሄደ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 29:1
17 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሎሌውም ከጌታው ግመሎች መካከል ዐሥር ግመሎችን ወስዶ፥ ከጌታውም ዕቃ መልካም መልካሙን ይዞ ተነሣ፥ ተነሥቶም ወደ መስጴጦምያ ወደ ናኮር ከተማ ሄደ።


ይስሐቅም አርባ ዓመት ሲሆነው ርብቃን አገባ፥ እርሷም በመስጴጦምያ የሚኖሩ የሶርያዊው የባቱኤል ልጅና የሶርያዊው የላባ እኅት ናት።


ነገር ግን የአብርሃም ለነበሩትም ለቁባቶቹ ልጆች አብርሃም ስጦታ ሰጣቸው፥ እርሱም ገና በሕይወቱ ሳለ ከልጁ ከይስሐቅ ለይቶ ወደ ፀሐይ መውጫ ወደ ምሥራቅ አገር ሰደዳቸው።


እግዚአብሔርም ያዕቆብን አለው፦ “ተነሥተህ ወደ ቤቴል ውጣ፥ በዚያም ኑር፥ ከወንድምህ ከዔሳው ፊት በሸሸህ ጊዜ ለተገለጠልህ ለእግዚአብሔርም መሠውያውን ሥራ።”


በዚያም መሠዊያውን ሠራ፥ የዚያንም ቦታ ስም “ኤልቤቴል” ብሎ ጠራው፥ እርሱ ከወንድሙ ፊት በሸሸበት ጊዜ እግዚአብሔር በዚያ ተገልጦለት ነበርና።


ሰሎሞን ከምሥራቅ አገርና ከግብጽም ጥበበኞች እጅግ የላቀ ጥበብ ነበረው።


ልቤን ባሰፋኸው ጊዜ፥ በትእዛዞችህ መንገድ ሮጥሁ።


ትእዛዝህን ለመጠበቅ ጨከንሁ አልዘገየሁምም።


እግዚአብሔር ሥራህን ተቀብሎታልና ሂድ፥ እንጀራህን በደስታ ብላ፥ የወይን ጠጅህንም በተድላ ጠጣ።


ኃጢአት በገለዓድ አለ፤ ፈጽመው ከንቱ ናቸው፤ በሬዎችን በጌልገላ ይሠዋሉ፥ መሠዊያዎቻቸውም በእርሻ ትልሞች ላይ የድንጋይ ክምር ይሆናሉ።


በለዓምም ምሳሌውን ይመስል ጀመር፥ እንዲህም አለ፦ “ባላቅ ከአራም አመጣኝ፥ የሞዓብ ንጉሥ ከምሥራቅ ተራሮች፤ ‘ና፥ ያዕቆብን ርገምልኝ፤ ና፥ እስራኤልን አውግዝልኝ አለኝ።’


እስራኤላውያን ዘር በሚዘሩበት ጊዜ ሁሉ ምድያማውያን፥ አማሌቃውያንና ሌሎች የምሥራቅ ሕዝቦች መጥተው አገሩን ይወሩ ነበር።


በዚህ ጊዜ ምድያማውያን ሁሉ፥ አማሌቃውያንና ሌሎች የምሥራቅ ሕዝቦች ያላቸውን አስተባብረው የዮርዳኖስን ወንዝ በመሻገር በኢይዝራኤል ሸለቆ ሰፈሩ።


ብዛታቸው እንደ አንበጣ መንጋ የሆነ ምድያማውያን፥ አማሌቃውያንና ሌሎችም የምሥራቅ ሕዝቦች በሸለቆው ውስጥ ሰፍረው ነበር፤ የግመሎቻቸውም ብዛት በባሕር ዳርቻ እንዳለ አሸዋ ስፍር ቍጥር አልነበረውም።


በዚህ ጊዜ ዜባሕና ጻልሙና ዐሥራ አምስት ሺህ ከሆነ ሠራዊታቸው ጋር ቀርቀር በተባለ ስፍራ ነበሩ፤ ይህም ከምሥራቅ ሕዝቦች ከተውጣጣውና በጦር ሜዳ ከወደቀው መቶ ሃያ ሺህ ሰይፍ ታጣቂ ሠራዊት የተረፈው ነበር።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች