Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 28:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ያዕቆብም እንዲህ ብሎ ስእለት ተሳለ፦ “እግዚአብሔር ከእኔ ጋር ቢሆን፥ በምሄድባትም በዚች መንገድ ቢጠብቀኝ፥ የምበላውንም እንጀራ የምለብሰውንም ልብስ ቢሰጠኝ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ከዚያም ያዕቆብ እንዲህ ሲል ተሳለ፤ “እግዚአብሔር ከእኔ ጋራ ቢሆን በምሄድበትም መንገድ ቢጠብቀኝ፣ የምበላው ምግብ፣ የምለብሰው ልብስ ቢሰጠኝ

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ከዚህ በኋላ ያዕቆብ እንዲህ ብሎ ለእግዚአብሔር ተሳለ፦ “ከእኔ ጋር ሆነህ በምሄድበት መንገድ ብትጠብቀኝ፥ የሚያስፈልገኝን ምግብና ልብስ ብትሰጠኝ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ያዕ​ቆ​ብም እን​ዲህ ብሎ ስእ​ለት ተሳለ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእኔ ጋር ቢሆን፥ በም​ሄ​ድ​ባ​ትም በዚች መን​ገድ ቢጠ​ብ​ቀኝ፥ የም​በ​ላ​ው​ንም እን​ጀራ፥ የም​ለ​ብ​ሰ​ው​ንም ልብስ ቢሰ​ጠኝ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 ያዕቆብም እንዲህ ብሎ ስእለት ተሳለ፦ እግዚአብሔር ከእኔ ጋር ቢሆን በምሄድባትም በዚች መንገድ ቢጠብቀኝ

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 28:20
29 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ነገር ግን ምግብና ልብስ ካሉን እነዚህ ይበቁናል።


እኔ አገልጋይህ በሶርያ ምድር በገሹር ሳለሁ ‘ጌታ ወደ ኢየሩሳሌም የመለሰኝ እንደሆነ፥ በኬብሮን ለጌታ እሰግዳለሁ’ ብዬ ተስያለሁ።”


እኛ ሁላችንም ከሙላቱ ተቀበልን፥ በጸጋ ላይ ጸጋን፤


ከሚቃጠል መሥዋዕት ጋር ወደ ቤትህ እገባለሁ፥ በመከራዬ ጊዜ በአፌ የተናገርሁትን በከንፈሮቼም ቃል የገባሁልህን ስእለቴን እፈጽማለሁ።


ሐውልት የቀባህበት እና ለእኔ ስእለት የተሳልህበት የቤቴል አምላክ እኔ ነኝ፥ አሁንም ተነሥተህ ከዚህ ምድር ውጣ፥ ወደ ተወለድህበትም ምድር ተመለስ።’”


ከዚህም በኋላ ጳውሎስ እጅግ ቀን ተቀምጦ ወንድሞችንም ተሰናብቶ በመርከብ ወደ ሶርያ ሄደ፤ ስለትም ነበረበትና ራሱን በክንክራኦስ ተላጨ፤ ጵርስቅላና አቂላም ከእርሱ ጋር ነበሩ።


ለጌታ እንደማለ፥ ለያዕቆብም ኀያል እንደ ተሳለ፦


የጽድቅህን ፍርድ እጠብቅ ዘንድ ማልሁ፥ አጸናሁም።


በሕዝቡ ሁሉ ፊት ስእለቴን ለጌታ እፈጽማለሁ፥


በሕዝቡ ሁሉ ፊት፥ እነሆ ስእለቴን ለጌታ እፈጽማለሁ።


የሰውም ቁጣ ሳይቀር ክብርህን ይገልጣል፥ ከዚህ የሚተርፈውንም ትታጠቀዋለህ።


በእግዚአብሔር ፊት ለዘለዓለም ይኖራል፥ ይጠብቁት ዘንድ ቸርነትንና እውነትን አዘጋጅለት።


በድንኳንህ ለዘለዓለም እኖራለሁ፥ በክንፎችህም ጥላ እጋረዳለሁ፥


በእግዚአብሔር ታመንሁ፥ አልፈራም፥ ሰው ምን ያደርገኛል?


በዚያም ቀን ጌታ ለግብጻዊያን ራሱን ይገልጣል፤ ግብጻውያንም ጌታን ያውቃሉ፤ በመሥዋዕትና በእህል ቁርባንም ያመልኩታል፤ ለጌታም ስእለት ይሳላሉ፤ የተሳሉትንም ይፈጽማሉ።


የችግረኛን ችግር አልናቀምና፥ ቸልም አላለምና፥ ፊቱንም አልሰወረምና፥ ነገር ግን ወደ እርሱ በጮኸ ጊዜ ሰማው።


ሳኦል፥ “ዛሬ ጠላቶቼን ከመበቀሌ በፊት፥ እስከ ማታ ድረስ እህል የሚበላ ሰው የተረገመ ይሁን” ብሎ ሕዝቡን አስምሎ ስለ ነበር፥ በዚያች ዕለት የእስራኤል ሰዎች ተጨንቀው ዋሉ፤ ስለዚህ ከሕዝቡ አንድም እህል የቀመሰ አልነበረም።


ስለዚህ እኔም ለጌታ እሰጠዋለሁ፤ በሕይወት ዘመኑም ሁሉ ለጌታ የተሰጠ ይሆናል።” እርሱም በዚያ ለጌታ ሰገደ።


እንዲህም ብላ ስእለት ተሳለች፤ “የሠራዊት ጌታ ሆይ፤ የአገልጋይህን መዋረድ ተመልክተህ ብታስበኝ፥ ለአገልጋይህም ወንድ ልጅ ብትሰጣት፥ በሕይወት ዘመኑ ሁሉ ለጌታ እሰጠዋለሁ፤ ምላጭም በራሱ ላይ አያርፍም።”


እነሆም እኔ ከአንተ ጋር ነኝ፥ በምትሄድባትም መንገድ ሁሉ እጠብቅሃለሁ፥ ወደዚችም ምድር እመልስሃለሁ፥ የነገርሁህን ሁሉ እስካደርግልህ ድረስ አልተውህምና።”


ተነሥተንም ወደ ቤቴል እንውጣ፥ በዚያም በመከራዬ ጊዜ ለሰማኝ፥ በሄድሁበትም መንገድ ከእኔ ጋር ለነበረው ለእግዚአብሔር መሠውያን እሠራለሁ።”


ያቤጽም፦ “እባክህ፥ መባረክን ባርከኝ፥ አገሬንም አስፋው፤ እጅህም ከእኔ ጋር ይሁን፤ እንዳይጎዳኝም ከክፋት ጠብቀኝ” ብሎ የእስራኤልን አምላክ ጠራ፤ እግዚአብሔርም የለመነውን ሰጠው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች