Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 28:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 እነሆም እኔ ከአንተ ጋር ነኝ፥ በምትሄድባትም መንገድ ሁሉ እጠብቅሃለሁ፥ ወደዚችም ምድር እመልስሃለሁ፥ የነገርሁህን ሁሉ እስካደርግልህ ድረስ አልተውህምና።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 እኔ ከአንተ ጋራ ነኝ፤ በምትሄድበት ስፍራ ሁሉ እጠብቅሃለሁ፤ ወደዚህችም ምድር እመልስሃለሁ፤ የሰጠሁህን ተስፋ እስከምፈጽምልህ ድረስ አልተውህም።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 አይዞህ፥ እኔ ከአንተ ጋር ነኝ፤ በምትሄድበትም ስፍራ ሁሉ እጠብቅሃለሁ፤ ወደዚህም ምድር በደኅና እመልስሃለሁ፤ የገባሁልህን ቃል ኪዳን ሁሉ እፈጽምልሃለሁ፤ ከቶም አልተውህም።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 እነ​ሆም፥ እኔ ከአ​ንተ ጋር እሄ​ዳ​ለሁ፤ በም​ት​ሄ​ድ​በ​ትም መን​ገድ ሁሉ እጠ​ብ​ቅ​ሃ​ለሁ፤ ወደ​ዚ​ያ​ችም ምድር እመ​ል​ስ​ሃ​ለሁ፤ የነ​ገ​ር​ሁ​ህን ሁሉ እስ​ካ​ደ​ር​ግ​ልህ ድረስ አል​ተ​ው​ህ​ምና።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 እነሆም እኔ ከአንተ ጋር ነኝ በምትሄድባትም ምድር እመልስሃለሁ የነገርሁህን ሁሉ እስካደርግልህ ድርስ አልተውህምና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 28:15
48 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በሕይወትህ ዘመን ሁሉ ማንም አይቋቋምህም፤ ከሙሴ ጋር እንደ ነበርሁ እንዲሁ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤ አልጥልህም፥ አልተውህምም።


እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ፤ እኔ አምላክህ ነኝና አትደንግጥ፤ አበረታሃለሁ፥ እረዳሀለሁ፥ በጽድቄም ቀኝ ደግፌ እይዝሃለሁ።


ከአንተም ጋር ይዋጋሉ፥ ነገር ግን አንተን ላድንህ እኔ ከአንተ ጋር ነኝና ድል አይነሡህም፥ ይላል ጌታ።”


ብርቱና ደፋር ሁኑ፤ አትፍሯቸው ወይም አትደንግጡላቸው። ጌታ አምላክህም ካንተ ጋር ይሄዳልና፤ አይተውህም፤ አይጥልህምም።”


በዚያችም ሌሊት ጌታ ተገለጠለት፥ እንዲህም አለው፦ “እኔ የአባትህ የአብርሃም አምላክ ነኝ፥ አትፍራ፥ እኔ ከአንተ ጋር ነኝና፥ እባርክሃለሁ፥ ስለ ባርያዬ ስለ አብርሃም ዘርህን አበዛለሁ።”


በዚህን ጊዜ ጌታ ያዕቆብን፥ “ወደ አባቶችህ ምድር እና ወደ ዘመዶችህ ተመለስ፥ ከአንተም ጋር እሆናለሁ” አለው።


በዚህች ምድር ተቀመጥ፥ ከአንተ ጋርም እሆናለሁ፥ እባርክሃለሁም፥ እነዚህን ምድሮች ሁሉ ለአንተም ለዘርህም እሰጣለሁና፥ ለአባትህ ለአብርሃም የማልሁለትንም መሐላ አጸናለሁ።


ሰማይና ምድር ያልፋሉ፤ ቃሌ ግን አያልፍም።


ሁለት ወይም ሦስት በስሜ በሚሰበሰቡበት በዚያ በመካከላቸው አለሁና።”


በውኃ ውስጥ ባለፍህ ጊዜ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፥ በወንዞችም ውስጥ ባለፍህ ጊዜ አያሰምጡህም፤ በእሳትም ውስጥ በሄድህ ጊዜ አትቃጠልም፤ ነበልባሉም አይፈጅህም።


አምላካችን እግዚአብሔር ከቀድሞ አባቶቻችን ጋር እንደ ነበረ ሁሉ ከእኛ ጋርም ይኑር፤ ምንጊዜም፤ አይተወንም፤ አይጥለንም፤


አሕዛብ ተናወጡ መንግሥታትም ተረበሹ፥ እርሱ ቃሉን ሰጠ፥ ምድርም ተንቀጠቀጠች።


ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ አስተምሩአቸው፤ እነሆ እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።”


ሰውነትን አካላዊ እንቅስቃሴ ማለማመድ መጠነኛ ጠቀሜታ ቢኖረውም እንኳ እግዚአብሔርን መምሰል ግን የአሁንና የሚመጣውን ሕይወት የተስፋ ቃል ስላለው፥ ለሁሉ ነገር ይጠቅማል።


ሐሰትን ይናገር ዘንድ እግዚአብሔር ሰው አይደለም፥ ይጸጸትም ዘንድ የሰው ልጅ አይደለም። እርሱ ያለውን አያደርገውምን? የተናገረውንስ አይፈጽመውምን?


እስራኤልም ዮሴፍን፦ “እነሆ እኔ እሞታለሁ፥ እግዚአብሔርም ከእናንተ ጋር ይሆናል፥ ወደ አባቶቻችሁም ምድር ይመልሳችኋል፥


ተመካከሩ፤ ግን አይሳካም፤ ዕቅድ አውጡ፤ ሆኖም አይጸናም፤ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነውና።


ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነሆ፤ ድንግል ትፀንሳለች፤ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፤ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች።


ጌታም፥ “በእርግጥ እኔ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤ ምድያማውያንንም እንደ አንድ ሰው አድርገህ ትመታቸዋለህ” አለው።


የኢየሱስ ክርስቶስ ባርያና የያዕቆብ ወንድም ይሁዳ፥ በእግዚአብሔር አብ ለተወደዱትና በኢየሱስ ክርስቶስም ለተጠበቁት፥ ለተጠሩት፤


ዕረፉ፥ እኔም አምላክ እንደሆንሁ እወቁ፥ በአሕዛብ ዘንድ ከፍ ከፍ እላለሁ፥ በምድርም ላይ ከፍ ከፍ እላለሁ።


ይሁን እንጂ ዮሴፍ እዚያ እስር ቤት ባለበት ጊዜ ሁሉ፥ ጌታ ከእርሱ ጋር ነበረ፤ ቸርነቱንም አበዛለት፥ በወህኒ አዛዡም ዘንድ ሞገስን ሰጠው።


ጌታ ከዮሴፍ ጋር ነበረ፤ ኑሮው ተቃናለት፤ እርሱም በግብፃዊው አሳዳሪው ቤት ኖረ።


እርሱም፦ “እኔ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤ እኔም እንደ ላክሁህ ምልክትህ ይህ ይሆናል፤ ሕዝቡን ከግብጽ ባወጣህ ጊዜ በዚህ ተራራ ላይ እግዚአብሔርን ታገለግላላችሁ” አለ።


ከክፉ ነገር ሁሉ ያዳነኝ መልአክ፥ እርሱ እነዚህን ብላቴኖች ይባርክ፥ ስሜም የአባቶቼ የአብርሃምና የይስሐቅም ስም በእነርሱ ይጠራ፥ በምድርም መካከል ይብዙ።”


ያዕቆብም አለ፦ “የአባቴ የአብርሃም አምላክ ሆይ፥ የአባቴም የይስሐቅ አምላክ ሆይ፥ ‘ወደ ትውልድ አገርህ ወደ ተወለድህበትም ስፍራ ተመለስ፥ በጎነትንም አደርግልሃለሁ’ ያልኸኝ ጌታ ሆይ፥


እኔ ወደ ግብጽ አብሬህ እወርዳለሁ፥ ከዚያም ደግሞ እኔ አወጣሃለሁ፥ የዮሴፍም እጅ ዓይንህን ይሸፍናል።”


እግዚአብሔርም ከብላቴናው ጋር ነበረ፥ አደገም፥ በምድረ በዳም ተቀመጠ፥ ቀስተኛም ሆነ።


እንዲህም አላቸው፥ “አባታችሁ ከእኔ ጋር እንደ ቀድሞው እንደማይወደኝ አያለሁ፥ ነገር ግን የአባቴ አምላክ ከእኔ ጋር ነው።


ሐውልት የቀባህበት እና ለእኔ ስእለት የተሳልህበት የቤቴል አምላክ እኔ ነኝ፥ አሁንም ተነሥተህ ከዚህ ምድር ውጣ፥ ወደ ተወለድህበትም ምድር ተመለስ።’”


ተነሥተንም ወደ ቤቴል እንውጣ፥ በዚያም በመከራዬ ጊዜ ለሰማኝ፥ በሄድሁበትም መንገድ ከእኔ ጋር ለነበረው ለእግዚአብሔር መሠውያን እሠራለሁ።”


ጌታ ለአንተና ለአባቶችህም እንደማለ ወደ ከነዓናውያን ምድር ያመጣሃል ለአንተም ይሰጥሃል፤


ጌታ ይባርክህ፥ ይጠብቅህም፤


አንተም ጌታ አምላካችሁ እርሱ እግዚአብሔር እንደሆነ፥ ለሚወዱትም ትእዛዙንም ለሚጠብቁ ቃል ኪዳኑንና ምሕረቱን እስከ ሺህ ትውልድ ድረስ የሚጠብቅ የታመነ አምላክ እንደሆነ እወቅ፤


ጌታ አምላክህ ምርኮህን ይመልስልሃል፤ ይራራልሃልም፤ አንተን ከበተነበት አሕዛብ መካከል ጌታ እግዚአብሔር እንደገና ይሰበስብሃል።


ጌታ ራሱ በፊትህ ይሄዳል፤ ከአንተም ጋር ይሆናል፤ ፈጽሞ አይለይህም፤ አይተውህምም፤ አትፍራ፤ ተስፋም አትቁረጥ።”


ራሔልም ዮሴፍን ከወለደች በኋላ ያዕቆብ ላባን እንዲህ አለው፦ “ወደ ስፍራዬ ወደ አገሬም እመለስ ዘንድ አሰናብተኝ።


እኔም ለያዕቆብ የማልሁትን ቃል ኪዳኔን አስታውሳለሁ፤ እንዲሁም ለይስሐቅና ለአብርሃም የማልሁትንም ቃል ኪዳኔን አስታውሳለሁ፤ ምድሪቱንም አስታውሳለሁ።


እኔ አምላክ እንድሆናቸው አሕዛብ እያዩ ከግብጽ ምድር ካወጣኋቸው ከአባቶቻቸው ጋር ያለኝን ቃል ኪዳን ስለ እነርሱ አስታውሳለሁ፤ እኔ ጌታ ነኝ።”


በመንገድህ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ መላእክቱን ስለ አንተ ያዝዛቸዋልና፥


ነገር ግን፦ ‘የእስራኤልን ልጆች ከሰሜን ምድር ካሳደዳቸውም ምድር ሁሉ ያወጣ በሕያው ጌታ እምላለሁ!’ ይባላል፤ እኔም ለአባቶቻቸው ወደ ሰጠኋት ወደ ምድራቸው እመልሳቸዋለሁ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች