Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 26:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ከዚያም እልፍ ብሎ ሌላ ጉድጓድ አስቈፈረ፥ ስለ እርሷም አልተጣሉም፥ ስምዋንም “ርኆቦት” ብሎ ጠራት እንዲህ ሲል፦ “አሁን እግዚአብሔር አሰፋልን፥ በምድርም እንበዛለን።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ይሥሐቅም ያን ቦታ ትቶ ሌላ ስፍራ ላይ የውሃ ጕድጓድ አስቈፈረ፤ በዚህ ጊዜ ግን አንድም ሰው ጠብ አላነሣበትም፤ ስለዚህ ያን የውሃ ጕድጓድ፣ “አሁን እግዚአብሔር ሰፊ ቦታ ሰጥቶናል፤ እኛም በምድር ላይ እንበዛለን” ሲል ርኆቦት ብሎ ጠራው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ከዚያም እልፍ ብሎ ሌላ የውሃ ጒድጓድ ቈፈረ፤ በዚህኛው የውሃ ጒድጓድ ምክንያት ምንም ጠብ ስላልተነሣ “እነሆ፥ አሁን እግዚአብሔር ሰፊ ቦታ ሰጠን፤ በምድር ላይም እንበዛለን ሲል፥ ያንን ቦታ ‘ረሖቦት’ ” ብሎ ሰየመው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ከዚ​ያም እልፍ ብሎ ሌላ ጕድ​ጓድ ቈፈረ፤ ስለ እር​ስ​ዋም አል​ተ​ጣ​ሉ​ትም፤ ስም​ዋ​ንም “መር​ኅብ” ብሎ ጠራት፤ እን​ዲህ ሲል፥ “አሁን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አሰ​ፋ​ልን፤ በም​ድ​ርም አበ​ዛን።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ከዚያም እልፍ ብሎ ሌላ ጕድጓድ አስቋፈረ ስለ እርስዋም አልተጣሉም፤ ስምዋንም፥ ርኖቦት ብሎ ጠራት እንዲህ ሲል፦ አሁን እግዚአብሔር አሰፋልን በምድርም እንበዛለን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 26:22
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ነገር ግን የእስራኤል ትውልዶች ፍሬያማ ነበሩ፥ እጅግም በዙ፥ ተባዙም፥ እጅግም በረቱ፤ ምድሪቱም በእነርሱ ሞላች።


እጅግም አበዛሃለሁ፥ ሕዝብም አደርግሃለሁ፥ ነገሥታትም ከአንተ ይወጣሉ።


በተጨነቅሁ ጊዜ ጌታን ጠራሁት፥ መለሰልኝ፥ አሰፋልኝም።


እንደዚሁም፥ “መከራ በተቀበልኩበት ምድር እግዚአብሔር ፍሬያማ አደረገኝ” ሲል ሁለተኛ ልጁን ኤፍሬም አለው።


በመከራዬ ቀን ደረሱብኝ፥ ጌታ ግን ድጋፍ ሆነኝ።


ለመዘምራን አለቃ በበገናዎች፥ የዳዊት መዝሙር።


ሁሉን የሚችል አምላክም ለብዙ ሕዝብ ጉባኤ እንድትሆን ይባርክህ፥ ያፍራህ፥ ያብዛህ፥


ሌላ ጉድጓድም ማሱ፥ ስለ እርሷም ደግሞ ተጣሉ፥ ስምዋንም “ስጥና” ብሎ ጠራት።


የድንኳንሽን ስፍራ አስፊ፥ መጋረጃዎችሽንም ይዘርጉ፤ አትቈጥቢ፤ አውታሮችሽን አስረዝሚ ካስሞችሽንም አጽኚ።


በቀኝና በግራ ትስፋፊያለሽ፥ ዘርሽም አሕዛብን ይወርሳሉ፥ የፈረሱትንም ከተሞች መኖሪያ ያደርጋሉ።


ልቤን ባሰፋኸው ጊዜ፥ በትእዛዞችህ መንገድ ሮጥሁ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች