ዘፍጥረት 26:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)18 ይስሐቅም በአባቱ በአብርሃም ዘመን ቈፍረዋቸው የነበሩትን የውኃ ጉድጓዶች ደግሞ አስቈፈረ፥ አብርሃም ከሞተ በኋላ የፍልስጥኤም ሰዎች ደፍነዋቸው ነበሩና፥ አባቱም ይጠራቸው በነበረው ስም ጠራቸው። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም18 ይሥሐቅም በአባቱ በአብርሃም ጊዜ ተቈፍረው የነበሩትን፣ አባቱ ከሞተ በኋላ ፍልስጥኤማውያን የደፈኗቸውን የውሃ ጕድጓዶች እንደ ገና እንዲከፈቱ አደረገ፤ አባቱ ቀድሞ ባወጣላቸው ስምም መልሶ ጠራቸው። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም18 አብርሃም በሕይወት ሳለ አስቈፍሮአቸው የነበሩትንና አብርሃም ከሞተ በኋላ ግን ፍልስጥኤማውያን የደፈኑአቸውን የውሃ ጒድጓዶች ይስሐቅ እንደገና እንዲቈፈሩ አደረገ፤ አባቱ ባወጣላቸው ስሞችም ጠራቸው። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)18 ይስሐቅም የአባቱ የአብርሃም አገልጋዮች ቈፍረዋቸው የነበሩትን የውኃ ጕድጓዶች ደግሞ አስቈፈረ፤ አባቱ አብርሃም ከሞተ በኋላ የፍልስጥኤም ሰዎች ደፍነዋቸው ነበርና፤ አባቱም አብርሃም ይጠራቸው በነበረው ስም ጠራቸው። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)18 ይስሐቅም በአባቱ በአብርሃም ዘመን ቈፍረዋቸ የነበሩትን የውኃ ጕድጓዶች ደግሞ አስቈፈረ፤ አብርሃም ከሞተ በኍላ የፍልስጥኤም ሰዎች ደፍነዋቸው ነበሩን አባቱም ይጠራቸው በነብረው ስም ጠራቸው። ምዕራፉን ተመልከት |