ዘፍጥረት 24:54 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)54 እርሱም ከእርሱም ጋር ያሉት በሉ ጠጡም፥ ከዚያም አደሩ፥ ማልደውም ተነሡና፦ “ወደ ጌታዬ እሄድ ዘንድ አሰናብቱኝ” አላቸው። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም54 እርሱና ዐብረውት የነበሩ ሰዎችም በልተው፣ ጠጥተው እዚያው ዐደሩ። በማግስቱም ጧት ሲነሡ፣ የአብርሃም አገልጋይ፣ “እንግዲህ ወደ ጌታዬ እንድመለስ አሰናብቱኝ” አለ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም54 ከዚህ በኋላ የአብርሃም አገልጋይና አብረውት የነበሩ ሰዎች በልተው ጠጥተው እዚያው ዐደሩ፤ ጠዋት በተነሡ ጊዜ የአብርሃም አገልጋይ “እንግዲህ ወደ ጌታዬ እንድመለስ ፍቀዱልኝ” አለ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)54 ከዚህም ሁሉ በኋላ እርሱ፥ ከእርሱ ጋር ያሉትም በሉ፤ ጠጡም፤ በዚያም አደሩ፤ በማለዳም ተነሥቶ፥ “ወደ ጌታዬ እሄድ ዘንድ አሰናብቱኝ” አላቸው። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)54 እርሱም ከእርሱም ጋር ያሉት በሉ ጠጡም ከዚያም አደሩ ማልደውም ተነሡና፦ ወደ ጌታዬ እሄድ ዘንድ አሰናብቱኝ አላቸው። ምዕራፉን ተመልከት |