Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 24:52 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

52 የአብርሃምም ሎሌ ነገራቸውን በሰማ ጊዜ ወደ ምድር ወድቆ ለእግዚአብሔር ሰገደ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

52 የአብርሃም አገልጋይ ያሉትን በሰማ ጊዜ በምድር ላይ ተደፍቶ ለእግዚአብሔር ሰገደ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

52 የአብርሃም አገልጋይ ይህን በሰማ ጊዜ በጒልበቱ ተንበርክኮ ለእግዚአብሔር ሰገደ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

52 የአ​ብ​ር​ሃ​ምም ሎሌ ነገ​ራ​ቸ​ውን በሰማ ጊዜ ወደ ምድር ወድቆ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰገደ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

52 የአብርሃምም ሎሌ ነገራቸውን በሰማ ጊዜ ወደ ምድር ወድቆ ለእግዚአብሔር ሰገደ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 24:52
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሰውዬውም አጎነበሰ፥ ለእግዚአብሔርም ሰገደ።


በግምባሬም አጎነበስሁ፥ ለእግዚአብሔርም ሰገድሁ፥ የጌታዬን የወንድሙን ልጅ ለልጁ እወስድ ዘንድ በቀና መንገድ የመራኝን የጌታዬን የአብርሃምን አምላክ እግዚአብሔርን አመሰገንሁ።


ርብቃ እነኋት በፊትህ ናት፥ ይዘሃት ሂድ፥ እግዚአብሔር እንደ ተናገረ ለጌታህም ልጅ ሚስት ትሁን።”


ዳዊትም ጉባኤውን ሁሉ፦ “አምላካችሁን ጌታን ባርኩ” አላቸው። ጉባኤውም ሁሉ የአባቶቻቸውን አምላክ ጌታን ባረኩ፥ ራሳቸውንም አዘንብለው ለጌታና ለንጉሡ ሰገዱ።


ኢዮሣፍጥም በግንባሩ ወደ ምድር ሰገደ ይሁዳም ሁሉ በኢየሩሳሌምም የሚኖሩ በጌታ ፊት በምድር በግንባራቸው ተደፍተው ለጌታ ሰገዱ።


ኑ፥ እንስገድ ለእርሱም እንገዛ፥ በፈጠረን በእርሱ በጌታ ፊት እንበርከክ፥


ወደ ቤትም በገቡ ጊዜ ሕፃኑን ከእናቱ ከማርያም ጋር አዩት፤ ወድቀውም ሰገዱለት፤ ሣጥኖቻቸውንም ከፍተው እጅ መንሻ ወርቅ፥ ዕጣንና ከርቤ አቀረቡለት።


ስለዚህ እኔም ለጌታ እሰጠዋለሁ፤ በሕይወት ዘመኑም ሁሉ ለጌታ የተሰጠ ይሆናል።” እርሱም በዚያ ለጌታ ሰገደ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች