Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 24:44 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

44 እርሷም፦ ‘አንተ ጠጣ፥ ደግሞም ለግመሎችህ እቀዳለሁ የምትለኝ፥ እግዚአብሔር ለጌታዬ ልጅ ያዘጋጃት ሴት እርሷ ትሁን።’”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

44 “ዕሺ ጠጣ፤ ለግመሎችህም እቀዳላቸዋለሁ” የምትለኝ እርሷ እግዚአብሔር ለጌታዬ ልጅ የመረጣት ትሁን።’

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

44 እርስዋም ‘እሺ ጠጣ፤ ለግመሎችህም እቀዳላቸዋለሁ’ የምትለኝ ብትሆን፥ ለጌታዬ ልጅ ሚስት እንድትሆን አንተ የመረጥካት እርስዋ ትሁን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

44 እር​ስ​ዋም ፦ ‘አንተ ጠጣ፤ ደግ​ሞም ለግ​መ​ሎ​ችህ እቀ​ዳ​ለሁ’ የም​ት​ለኝ ድን​ግል፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለጌ​ታዬ ልጅ ለባ​ሪ​ያዉ ለይ​ስ​ሐቅ ያዘ​ጋ​ጃት ሚስት እር​ስዋ ትሁን። በዚ​ህም ለጌ​ታዬ ምሕ​ረ​ትን እን​ዳ​ደ​ረ​ግህ አው​ቃ​ለሁ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

44 እርስዋም፦ አንተ ጠጣ ደግሞም ለግመሎችህ እቀዳለሁ የምትለኝ እግዚአብሔር ለጌታዬ ልጅ ያዘጋጃት ሴት እርስዋ ትሁን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 24:44
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ውኃ እጠጣ ዘንድ እንስራሽን አዘንብዪ የምላት እርሷም አንተ ጠጣ፥ ግመሎችህን ደግሞ አጠጣለሁ የምትለኝ ቆንጆ፥ እርሷ ለባርያህ ለይስሐቅ ያዘጋጀሃት ትሁን፥ በዚህም ለጌታዬ ምሕረትን እንዳደረግህ አውቃለሁ።”


በመጨረሻም ሁላችሁ በአንድ ልብ ሁኑ፤ እርስ በእርሳችሁ ተሳሰቡ፤ በወንድማማችነት ፍቅር ተዋደዱ፤ ርኅሩኆችና ትሑታን ሁኑ።


እንግዶችን መቀበል አትርሱ፤ አንዳንዶች በዚህ ሳቢያ ሳያውቁ መላእክትን በእንግድነት ተቀብለዋል።


ይልቁንም እግዚአብሔርን እንፈራለን ለሚሉ ሴቶች እንደሚገባ መልካም ሥራን በመሥራት ይሁን።


ከበርቴ ሰው ግን ለመከበር ያስባል፤ ለመከበርም ጸንቶ ይኖራል።


ቤትና ባለጠግነት ከአባቶች ዘንድ ይወረሳሉ፥ አስተዋይ ሚስት ግን ከጌታ ዘንድ ናት።


ሚስት ያገኘ በረከትን አገኘ፥ ከጌታም ሞገስን ይቀበላል።


ዕጣ በጉያ ይጣላል፥ መደብዋ ሁሉ ግን ከጌታ ዘንድ ነው።


ከአዳም የወሰዳትንም አጥንት፥ ጌታ እግዚእብሔር፥ ሴት አድርጎ ሠራት፥ ወደ አዳምም አመጣለት።


እነሆ፥ እኔ በውኃው ምንጭ ላይ ቆሜአለሁ፥’ ውኃ ልትቀዳ ለምትመጣውም ቆንጆ፦ ‘ጥቂት ውኃ ከእንስራሽ አጠጪኝ’ ስላት፥


“እኔም የልቤን መናገር ገና ሳልፈጽም፥ እነሆ፥ ርብቃ እንስራዋን በትከሻዋ ተሸክማ ወጣች፥ ወደ ምንጭም ወርዳ ውኃ ቀዳች እኔም፦ ‘እስኪ አጠጪኝ’ አልኋት።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች