ዘፍጥረት 24:32 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)32 ሰውዬውም ወደ ቤት ገባ፥ ግመሎቹንም አራገፈ፥ ገለባና ገፈራም ለግመሎቹ አቀረበ፥ እግሩን ይታጠብ ዘንድ፥ ከእርሱም ጋር ላሉት ሰዎች እግር ውኃ አቀረበ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም32 ሰውየው ከላባ ጋራ ወደ ቤት ሄደ፤ የግመሎቹ ጭነት ተራግፎ ገለባና ድርቈሽ ተሰጣቸው፤ ለርሱና ዐብረውት ለነበሩት ሰዎች የእግር ውሃ ቀረበላቸው። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም32 ከዚህ በኋላ ሰውየው ወደ ቤት ሄደ፤ ላባም በግመሎቹ ላይ የነበረውን ጭነት አራግፎ ገለባና ድርቆሽ አቀረበላቸው፤ ቀጥሎም የአብርሃም አገልጋይና አብረውት የነበሩት ሰዎች እግራቸውን የሚታጠቡበት ውሃ አመጣላቸው። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)32 ሰውዬውም ወደ ቤት ገባ፤ ግመሎቹንም አራገፈ፤ ለግመሎቹም ሣርና ገለባ አቀረቡላቸው፤ እግሩን ይታጠብ ዘንድ ውኃ አመጡለት፤ ከእርሱ ጋር ላሉ ሰዎችም አመጡላቸው። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)32 ሰውዮውም ወደ ቤት ገባ ግመሎቹንም አራገፈ ገለባና ገፈራም ለግመሎቹ አቀረበ፤ እግሩን ይታጠብ ዘንድ ከእርሱም ጋር ላሉት ሰዎች እግር ውኃ አቀረበ። ምዕራፉን ተመልከት |