Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 24:31 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

31 እርሱም አለው፦ “አንተ የእግዚአብሔር ቡሩክ ግባ፥ ስለምን አንተ በውጪ ቆመሃል? እኔም ቤቱን ለግመሎችህም ስፍራ አዘጋጅቼአለሁ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

31 እርሱንም “አንተ የእግዚአብሔር ቡሩክ ሆይ፤ ና፤ እዚህ ውጭ የቆምኸው ለምንድን ነው? እነሆ፤ ለአንተ ማረፊያ ለግመሎችህም ማደሪያ አዘጋጅቻለሁ” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

31 ስለዚህ ላባ “አንተ እግዚአብሔር የባረከህ ሰው፥ ና ወደ ቤት እንሂድ፤ በውጪ የቆምከው ለምንድን ነው? በቤታችን ለአንተ ማረፊያ ስፍራ አለ፤ ለግመሎችህም ማደሪያ የተዘጋጀ ቦታ አለ” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

31 እር​ሱም አለው፥ “አንተ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቡሩክ፥ ግባ ስለ​ምን አንተ በውጪ ቆመ​ሃል? እኛም ቤትን፥ ለግ​መ​ሎ​ች​ህም ማደ​ሪ​ያን አዘ​ጋ​ጅ​ተ​ናል።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

31 እርሱም አለው፦ አንተ የእግዚአብሔር ቡሩክ ግባ፤ ስለምን አንተ በውጪ ቆመሃል? እኔም ቤቱን ለግመሎችህም ስፍራ አዘጋጅቼአለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 24:31
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

“አቤቱ፥ በፊትህስ ሞገስ አግኝቼ እንደሆነ ባርያህን አትለፈኝ ብዬ እለምናለሁ፥


“ጌቶቼ ሆይ፥ ወደ ባርያችሁ ቤት አቅኑ፥ ከዚያም እደሩ፥ እግራችሁንም ታጠቡ፥ ነገ ማልዳችሁም መንገዳችሁን ትሄዳላችሁ።” እነርሱም፦ “በአደባባዩ እናድራለን እንጂ፥ አይሆንም” አሉት።


እጅግም ዘበዘባቸው፥ ወደ እርሱም አቀኑ፥ ወደ ቤቱም ገቡ፥ ማዕድ አቀረበላቸው፥ ቂጣንም ጋገረ እነርሱም በሉ።


ቀለበቱንና አምባሮቹን በእኅቱ እጅ ባየ ጊዜ፥ የእኅቱን የርብቃንም ነገር፦ “ያ ሰው እንዲህ አለኝ” ያለችውን በሰማ ጊዜ፥ እርሱ ወደዚያ ሰው መጣ፥ እነሆም፥ በውኃው ምንጭ አጠገብ ከግመሎቹ ዘንድ ቆሞ ነበር።


እኛ አንተን እንዳልነካንህ፥ በጎነትንም ብቻ እንዳሳየንህ፥ በሰላምም እንደ ሰደድንህ፥ አንተም ክፉ እንዳትሠራብን፥ አንተ አሁንም ከጌታ ዘንድ የተባረክህ ነህ።”


ላባም የእኅቱን ልጅ የያዕቆብን ወሬ በሰማ ጊዜ ሊቀበለው ሮጠ፥ አቅፎም ሳመው፥ ወደ ቤቱም አገባው። ነገሩንም ሁሉ ለላባ ነገረው።


እናንተ ሰማይንና ምድርን በሠራ ጌታ የተባረካችሁ ሁኑ።


ገንዘብ ባደረገው ፊት መማለጃ እንደ ተዋበ ዕንቁ ነው፥ ወደ ዞረበትም ስፍራ ሁሉ ሥራውን ያቀናል።


የሰው ስጦታ መንገዱን ታሰፋለታለች፥ በታላላቆችም ፊት ታገባዋለች።


እናቱን፥ “አንድ ሺህ አንድ መቶ ሰቅል ብር ተሰርቆብሽ፥ የሰረቀውን ሰው ስትራገሚ ሰምቼሽ ነበር፤ ብሩ ከእኔ ዘንድ ይገኛል፤ የወሰድሁት እኔ ነኝ” አላት። ከዚያም እናቱ፥ “ልጄ፤ ጌታ ይባርክህ” አለችው።


ቦዔዝም አላት፦ “ልጄ ሆይ፥ በጌታ የተባረክሽ ሁኚ፥ ባለ ጠጋ ይሁን ወይም ድሀ፥ ወጣቶችን መርጠሽ መሄድ አልፈለግሽምና ከፊተኛው ይልቅ አሁን ባደረግሽው ታማኝነትን አድርገሻል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች