ዘፍጥረት 23:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)13 የአገሩ ሰዎችም እየሰሙ ለኤፍሮን እንዲህ ሲል ተናገረ፦ “ፈቃድህ ከሆነ፥ አድምጠኝ፤ የእርሻውን ዋጋ እሰጥሃለሁ፥ አንተም ከእኔ ተቀበለኝና የሚስቴን አስክሬን እዚያ ወስጄ ልቅበር” አለው። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም13 ሁሉም እየሰሙት ኤፍሮንን፣ “የዕርሻውን ቦታ ዋጋ ልክፈል፤ እባክህን ተቀበለኝና ሬሳዬን ልቅበርበት” አለው። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም13 ሁሉም እየሰሙ ዔፍሮንን “እባክህ አድምጠኝ፤ ቦታውን በሙሉ እገዛዋለሁ፤ እነሆ ዋጋውን ተቀበለኝና የሚስቴን አስከሬን እዚያ ወስጄ ልቅበር” አለው። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)13 የሀገሩ ሕዝብም ሲሰሙ ለኤፍሮን እንዲህ ሲል ተናገረ፥ “ከእኔ ቅርብ ነህና ስማኝ፤ የእርሻህንም ዋጋ ከእኔ ውሰድ፤ ሬሳዬንም በዚያ እቀብራለሁ።” ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)13 የአገሩ ሰዎችም ሲሰሙ ለኤፍሮን እንዲህ ሲል ተናገረ፦ ነገሬን ትሰማ ዘንድ እለምንሃለሁ፤ የእርሻውን ዋጋ እሰጥሃለሁ አንተም ከእኔ ዘንድ ውሰድ፥ ሬሳዬም፥ በዚይ እቀብራለሁ። ምዕራፉን ተመልከት |