Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 21:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ጌታም እንደ ተናገረው ሣራን አሰበ፥ እግዚአብሔርም እንደ ተናገረው ለሣራ አደረገላት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 እግዚአብሔር በተናገረው መሠረት ሣራን ዐሰባት፤ የገባውንም ተስፋ ፈጸመላት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ስለዚህ እግዚአብሔር በተናገረው መሠረት ለሣራ መልካም በማድረግ የገባውን ቃል ኪዳን ፈጸመላት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እንደ ተና​ገ​ረው ሣራን ጐበ​ኛት፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እንደ ተና​ገ​ረው ለሣራ አደ​ረ​ገ​ላት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 እግዚአብሔርም እንደ ተናገረው ሣራን አሰበ፤ እግዚአብሔርም እንደ ተናገረው ለሣራ አደረገላት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 21:1
23 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ስለ ምስኪኖች መከራ፥ ስለ ችግረኞች ጩኸት ጌታ፦ አሁን እነሣለሁ ይላል፥ የተጠሙትንም ደኅንነት አመጣላቸዋለሁ።


እርሱም፦ “የዛሬ ዓመት እንደ ዛሬው ጊዜ ወደ አንተ በእውነት እመለሳለሁ፥ ሚስትህ ሣራም ልጅን ታገኛለች” አለ። ሣራም በድንኳን ደጃፍ በስተ ኋላው ሳለች ይህንን ሰማች።


በውኑ ለጌታ የሚሳነው ነገር አለን? የዛሬ ዓመት እንደ ዛሬው ጊዜ ወደ አንተ እመለሳለሁ፥ ሣራም ልጅን ታገኛለች።”


እግዚአብሔርም አለ፦ “በእውነት ሚስትህ ሣራ ወንድ ልጅን ትወልድልሃለች፥ ስሙንም ይስሐቅ ብለህ ትጠራዋለህ፥ ከእርሱ በኋላ ለዘሩ የዘለዓለም ቃል ኪዳን እንዲሆን ቃል ኪዳኔን ከእርሱ ጋር አቆማለሁ።


ከቶውኑ የማይዋሽ እግዚአብሔር ከዘመናት በፊት ቃል በገባው የዘለዓለም ሕይወት ተስፋ ያደረገ፤


ነገር ግን የባርያይቱ ልጅ በሥጋ ልማድ ተወለደ፥ የነጻይቱ ልጅ ግን በተስፋው ቃል መሠረት ተወለደ።


ሰማይና ምድር ያልፋሉ፤ ቃሌ ግን አያልፍም።


ጌታም ሐናን አሰበ፤ እርሷም ፀነሰች፤ ሦስት ወንዶችና ሁለት ሴቶች ልጆች ወለደች። ብላቴናውም ሳሙኤል በጌታ ፊት አደገ።


ወንድሞች ሆይ! እናንተም እንደ ይስሐቅ የተስፋ ቃል ልጆች ናችሁ።


እርሷም በሞዓብ ምድር ሳለች ጌታም ሕዝቡን እንደ ጐበኘ እህልም እንደሰጣቸው ስለ ሰማች፥ ከሞዓብ ምድር ልትመለስ ከሁለቱ ምራቶችዋ ጋር ተነሣች።


ዮሴፍም ወንድሞቹን፦ “እኔ እሞታለሁ፥ እግዚአብሔርም መጎብኘትን ይጎበኛችኋል፥ ከዚህችም ምድር ያወጣችኋል፥ ለአብርሃምና ለይስሐቅ ለያዕቆብም ወደ ማለላቸው ምድር ያደርሳችኋል” አላቸው።


ቃል ኪዳኔን ግን በሚመጣው ዓመት በዚሁ ጊዜ ሣራ ከምትወልድልህ ከይስሐቅ ጋር አቆማለሁ።”


እባርካታለሁ፥ ደግሞም ከእርሷ ልጅ እሰጥሃለሁ፥ እባርካታለሁም፥ የአሕዛብም እናት ትሆናለች፥ የአሕዛብ ነገሥታት ከእርሷ ይወጣሉ።”


“የእስራኤል ጌታ አምላክ ይባረክ፤ ጐብኝቶ ለሕዝቡ ቤዛ አድርጎአልና፤


ሕዝቡም አመኑ፤ ጌታ የእስራኤልን ልጆች እንደተመለከተ ጭንቀታቸውንም እንዳየ በሰሙ ጊዜ፥ አጎነበሱ ሰገዱም።


አቤቱ፥ በሕዝብህ ሞገስ አስበኝ፥ በመድኃኒትህም ጐብኘኝ፥


አትስገድላቸው፥ አታምልካቸውም፤ እኔ ጌታ አምላክህ ቀናተኛ አምላክ ነኝና በሚጠሉኝ እስከ ሦስተኛና እስከ አራተኛ ትውልድ ድረስ የአባቶችን ኃጢአት በልጆች ላይ የማመጣ፥


ሂድ የእስራኤልንም ሽማግሌዎች ትሰበስባለህ እንዲህም ትላቸዋለህ፦ “ጌታ የአባቶቻችሁ አምላክ የአብርሃም አምላክ የይስሐቅ፥ የያዕቆብም ተገለጠልኝ፤ እንዲህም አለኝ ‘ጎበኘኋችሁ፥ በግብጽም የሚደረግባችሁን አየሁ፤


አንቺንም በአንቺም ውስጥ የሚኖሩትን ልጆችሽን በምድር ላይ ይጨፈልቃሉ፤ በአንቺ ውስጥም በድንጋይ ላይ የሚኖር ድንጋይ አያስቀሩም፤ የተጐብኘሽበትን ዘመን አላወቅሽምና።”


ሣራም የጌታዬ ሚስት በእርጅናው ለጌታዬ ወንድ ልጅን ወለደች፥ የነበረውንም ሁሉ ሰጠው።


በማግስቱ ጠዋት ተነሥተው በጌታ ፊት ሰገዱ፤ ከዚያም በራማ ወደሚገኘው ቤታቸው ተመለሱ። ሕልቃናም ሚስቱን ሐናን ዐወቃት፤ ጌታም አሰባት፤


ነገር ግን ሴቲቱ ፀነሰች፤ ልክ ኤልሳዕ የተናገረው ጊዜ ሲደርስ በተከታዩ ዓመት ወንድ ልጅ ወለደች።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች