Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 19:37 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

37 ታላቂቱም ወንድ ልጅ ወለደች ስሙንም ሞዓብ ብላ ጠራችው፥ እርሱም እስከ ዛሬ የሞዓባውያን አባት ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

37 ትልቋ ልጁ ወንድ ልጅ ወለደች፤ ስሙንም ሞዓብ ብላ ጠራችው፤ እርሱም የዛሬዎቹ ሞዓባውያን አባት ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

37 ታላቂቱ ወንድ ልጅ ወለደችና ስሙን ሞአብ አለችው፤ እርሱ ዛሬ ሞአባውያን ተብለው ለሚጠሩት ሕዝቦች ቅድመ አያት ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

37 ታላ​ቂ​ቱም ወንድ ልጅ ወለ​ደች፤ ስሙ​ንም ሞዓብ ብላ ጠራ​ችው፤ ይህም ከአ​ባቴ የወ​ለ​ድ​ሁት ማለት ነው። እር​ሱም እስከ ዛሬ የሞ​ዓ​ባ​ው​ያን አባት ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

37 ታላቂቱም ውንድ ልጅ ወለደች ስሙንም ሞዓብ ብላ ጠራችው እርሱም እስከ ዛሬ የሞዓባውያን አባት ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 19:37
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የሎጥም ሁለቱ ሴቶች ልጆች ከአባታቸው ፀነሱ።


አሦርም ከእነርሱ ጋር ተባበረ፥ ለሎጥ ልጆችም ረዳት ሆኗቸው።


የሞዓብን ማላገጥና የአሞንን ልጆች ስድብ ሰምቻለሁ፤ በሕዝቤም ላይ አላግጠዋል፥ በድንበራቸውም ላይ ኮርተዋል።


ሞዓብ ሆይ! ወዮልህ! የካሞሽ ሕዝብ ሆይ! ጠፋህ፤ ወንዶች ልጆቹን ለሽሽት፥ ሴቶች ልጆቹንም ለምርኮ፥ ለአሞራውያን ንጉሥ ለሴዎን ሰጠ።


በአሞን ልጆች አቅራቢያ ስትደርስ፥ ለሎጥም ልጆች ርስት አድርጌ ስለ ሰጠሁ ከአሞን ልጆች ምድር ርስት አልሰጥህምና፥ አትጣላቸው አትውጋቸውም።’”


ጌታም አለኝ፦ ‘እኔ ዔርን ለሎጥ ልጆች ርስት አድርጌ ስለ ሰጠሁ፥ ከእነርሱ ምድር ምንም አልሰጣችሁምና ሞዓባውያንን አትጣላ በውጊያም አትጋፈጣቸው።’”


“አሞናዊም ሆነ ሞዓባዊ ወይም ማናቸውም የእርሱ ዘር፥ እስከ ዐሥር ትውልድ እንኳን ቢሆን ወደ ጌታ ጉባኤ አይግባ።


ደግሞም የምዋቹ ስም ከወንድሞቹ መካከል ከአገሩም ደጅ እንዳይጠፋ፥ የምዋቹን ስም በርስቱ ላይ እንዳስነሣ የመሐሎንን ሚስት ሞዓባዊቱን ሩትን ሚስት ትሆነኝ ዘንድ ወሰድሁአት፥ እናንተም ዛሬ ምስክሮች ናችሁ” አላቸው።


ሳኦል በእስራኤል ላይ ከነገሠ በኋላ፥ በዙሪያው ያሉትን ጠላቶቹን ሞዓብን፥ አሞናውያንን፥ ኤዶምን፥ የጾባን ነገሥታትና ፍልስጥኤማውያንን ወጋቸው። በተዋጋበት ስፍራ ሁሉ ድል አድራጊ ነበር።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች