ዘፍጥረት 19:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)15 ጎህም በቀደደ ጊዜ መላእክት ሎጥን፦ “ተነሣ፥ ሚስትህንና ከዚህ ያሉትን ሁለቱን ሴቶች ልጆችህን ውሰድ፥ በከተማይቱ ኃጢአት እንዳትጠፋ” እያሉ ያስቸኩሉት ነበር። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም15 ሲነጋጋም መላእክቱ ሎጥን፣ “ከከተማዪቱ ጋራ ዐብራችሁ እንዳትጠፉ፣ ሚስትህንና ሁለቱን ሴት ልጆችህን ይዘህ ከዚህ ቦታ በፍጥነት ውጣ” ብለው አቻኰሉት። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም15 በማግስቱ ጠዋት በማለዳ መላእክቱ ሎጥን “ፍጠን! ከተማይቱ ስትጠፋ አብራችሁ እንዳትጠፉ ሚስትህንና ሁለቱን ሴቶች ልጆችህን ይዘህ ከዚህ ውጣ” እያሉ አጣደፉት። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)15 ጎህም በቀደደ ጊዜ መላእክት ሎጥን፥ “ተነሣ፤ ሚስትህንና ከዚህ ያሉትን ሁለቱን ሴቶች ልጆችህን ውሰድ፤ አንተም በከተማዪቱ ሰዎች ኀጢአት እንዳትጠፋ” እያሉ ያስቸኩሉት ነበር። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)15 ጎህም በቀደደ ጊዜ መላእክት ሎጥን፥ ተነሣ ሚስትህንና ከዚህ ያሉትን ሁለቱን ሴቶች ልጆችህን ውስድ በከተማይቱ ኃጢአት እንዳትጠፉ እያሉ ያስቸኵሉት ነበር። ምዕራፉን ተመልከት |