Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 18:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 በውኑ ለጌታ የሚሳነው ነገር አለን? የዛሬ ዓመት እንደ ዛሬው ጊዜ ወደ አንተ እመለሳለሁ፥ ሣራም ልጅን ታገኛለች።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር አለን? ጊዜው ሲደርስ እመለሳለሁ፤ ሣራም ልጅ ይኖራታል።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ከቶ ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር አለን? እንደ ነገርኩህ የዛሬ ዓመት በዚህ ጊዜ ተመልሼ እመጣለሁ፤ በዚያን ጊዜ ሣራ ወንድ ልጅ ትወልዳለች” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 በውኑ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ሳ​ነው ነገር አለን? የዛሬ ዓመት እንደ ዛሬው ጊዜ ወደ አንተ እመ​ለ​ሳ​ለሁ፤ ሣራም ልጅን ታገ​ኛ​ለች።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 በውኑ ለእግዚአሔር የሚሳነው ነገር አለን? የዛሬ ዓመት እንድ ዛሬው ጊዜ ወደ አንተ እመለሳለሁ፤ ሣራም ልጅን ታግኝለች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 18:14
38 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ለእግዚአብሔር የሚሳነው አንዳች ነገር የለምና።”


ኢየሱስ ግን አያቸውና እንዲህ አላቸው “ይህ በሰው ዘንድ የማይቻል ነው፤ በእግዚአብሔር ዘንድ ግን ሁሉ ይቻላል።”


ኢየሱስም አያቸውና፥ “ይህ በሰው ዘንድ አይቻልም፤ በእግዚአብሔር ዘንድ ግን እንዲህ አይደለም፤ በእግዚአብሔር ዘንድ ሁሉ ይቻላል” አላቸው።


እነሆ፥ እኔ የሥጋ ለባሽ ሁሉ አምላክ የሆንሁ ጌታ ነኝ፤ በውኑ ለእኔ የሚሳነኝ ነገር አለን?


እንግዲህ በእኛ እንደሚሠራው ኃይል መጠን ከምንለምነው ወይም ከምናስበው ሁሉ ይልቅ እጅግ አብልጦ ማድረግ ለሚቻለው፥


“ሁሉንም ማድረግ እንድምትችል፥ ሐሳብህም ሊከለከል ከቶ እንደማይቻል አወቅሁ።


ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን ነገር ማድረግ እችላለሁ።


‘አቤቱ ጌታ ሆይ! ወዮ! እነሆ፥ በእውነት አንተ ሰማይንና ምድርን በታላቅ ኃይልህና በተዘረጋች ክንድህ ፈጥረሃል፥ ለአንተም ከቶ የሚሳንህ ምንም ነገር የለም።


የሰጠውንም ተስፋ እንደሚፈጽም ጽኑ እምነት ነበረው።


ጌታም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “በውኑ ጌታ ለዚህ እጅ አጥሮት ነውን? አሁን ቃሌ ለአንተ ይፈጸም ወይስ አይፈጸም እንደሆነ አንተ ታያለህ።”


ኤልሳዕም “በመጪው ዓመት ልክ ይህን ጊዜ ወንድ ልጅ ትታቀፊያለሽ” አላት። እርሷም፦ “አይደለም! ጌታዬ የእግዚአብሔር ሰው ሆይ! እባክህ የማይፈጸም የተስፋ ቃል አትንገረኝ!” አለችው።


ጌታ አምላክህ፥ ታላቅና የሚያስፈራ አምላክ፥ በመካከልህ ነውና በእነርሱ የተነሣ ልትደናገጥ አይገባም።


ኢየሱስም ወዲያው እጁን ዘርግቶ ያዘውና “አንተ እምነት የጎደለህ፥ ለምን ተጠራጠርህ?” አለው።


የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ በዚህ ወራት በዚህ በተረፈው ሕዝብ ዐይን ነገሩ ቢያስደንቅ፥ በውኑ ለእኔ ግን አስደናቂ ይሆናልን? ይላል የሠራዊት ጌታ።


በደልን ይቅር የሚል፥ የርስቱን ትሩፍ ዓመጽ የሚያሳልፍ እንደ አንተ ያለ አምላክ ማን ነው? ርኅራኄ ይወድዳልና ቁጣውን ለዘለዓለም አያቆይም።


ጌታ ታላቅ አምላክ ነውና፥ በአማልክትም ሁሉ ላይ ታላቅ ንጉሥ ነውና።


ጌታ አምላክህ ምርኮህን ይመልስልሃል፤ ይራራልሃልም፤ አንተን ከበተነበት አሕዛብ መካከል ጌታ እግዚአብሔር እንደገና ይሰበስብሃል።


እርሱም፦ “የዛሬ ዓመት እንደ ዛሬው ጊዜ ወደ አንተ በእውነት እመለሳለሁ፥ ሚስትህ ሣራም ልጅን ታገኛለች” አለ። ሣራም በድንኳን ደጃፍ በስተ ኋላው ሳለች ይህንን ሰማች።


መልአኩ ግን እንዲህ አለው፦ “ዘካርያስ ሆይ! ጸሎትህ ተሰምቶልሃልና አትፍራ፤ ሚስትህ ኤልሳቤጥም ወንድ ልጅ ትወልድልሃለች፤ ስሙንም ዮሐንስ ብለህ ትጠራዋለህ።


እነሆ፥ እግዚአብሔር ኃያል ነው፥ ማንንም አይንቅም፥ እርሱም በጥበባዊ ኃይሉም ጽኑ ነው።


ቃል ኪዳኔን ግን በሚመጣው ዓመት በዚሁ ጊዜ ሣራ ከምትወልድልህ ከይስሐቅ ጋር አቆማለሁ።”


እግዚአብሔር ከሙታን እንኳ ሊያስነሣው እንደሚችል አስቦአልና፤ ይስሐቅን እንደ ምሳሌ መልሶ ተቀበለ።


ኢየሱስ ግን ይህን ሰምቶ ለኢያኢሮስ መልሶ እንዲህ አለው፦ “አትፍራ፤ እመን ብቻ፤ እርሷም ትድናለች።”


ዮናታን ወጣት ጋሻ ጃግሬውን፥ “ና፤ ወደነዚያ ያልተገረዙ ሰዎች ጦር ሰፈር እንሻገር፤ ምናልባትም ጌታ ይዋጋልን ይሆናል፤ በብዙም ሆነ በጥቂት ለማዳን ጌታን የሚያግደው የለምና” አለው።


እርሱም ደግሞ ለራሱ ሁሉን ነገር በሥሩ ለማስገዛት በሚችልበት ኃይሉ ክቡር ሥጋውን እንዲመስል የተዋረደውን ሥጋችንን ይለውጣል።


ዘካርያስም መልአኩን፦ “እኔ ሽማግሌ ነኝ፤ ሚስቴም በዕድሜዋ ገፍታለችና ይህንን በምን አውቃለሁ?” አለው።


በልባችሁ ‘አብርሃም አባት አለን’ ብላችሁ አታስቡ፤ እግዚአብሔር ከእነዚህ ድንጋዮች ለአብርሃም ልጆች ሊያስነሣለት ይችላል እላችኋለሁ።


ጌታ ነገሠ፥ ግርማን ተጐናጸፈ፥ ጌታ ኃይልን ለበሰ፥ ታጠቀም፥ ዓለምን እንዳትናወጥ አጸናት።


አቤቱ፥ ተመለስ፥ እስከ መቼስ ነው? ለአገልጋዮችህ ራራ።


እግዚአብሔርም አብርሃምን አለው፦ “ካረጀሁ በኋላ በውኑ እወልዳለሁን? ስትል ሣራ ለምን ሳቀች?


ሣራም ስለ ፈራች፦ “አልሳቅሁም” ስትል ካደች። እርሱም፦ “አይደለም፥ ሳቅሽ እንጂ” አላት።


ጌታም እንደ ተናገረው ሣራን አሰበ፥ እግዚአብሔርም እንደ ተናገረው ለሣራ አደረገላት።


ሣራም ፀነሰች፥ እግዚአብሔርም በተናገረው ወራት ለአብርሃም በእርጅናው ወንድ ልጅን ወለደችለት።


በመጣሁስ ጊዜ ሰው ስለምን አልነበረም? በጠራሁስ ጊዜ የሚመልስ ስለምን አልነበረም? መታደግ እንዳትችል እጄ አጭር ሆናለችን? ወይስ ለማዳን ኃይል የለኝም? እነሆ፥ በገሠጽሁ ጊዜ ባሕርን አደርቃለሁ፥ ወንዞችንም ምድረ በዳ አደርጋቸዋለሁ፤ ውኃም አጥተው ዓሦቻቸው ይገማሉ፥ በጥማትም ይሞታሉ።


እባርካታለሁ፥ ደግሞም ከእርሷ ልጅ እሰጥሃለሁ፥ እባርካታለሁም፥ የአሕዛብም እናት ትሆናለች፥ የአሕዛብ ነገሥታት ከእርሷ ይወጣሉ።”


የጌታም መልአክ ለሴቲቱ ተገልጦ እንዲህ አላት፤ “እነሆ፤ አንቺ መካን ነሽ፤ ልጅም አልወለድሽም፤ ነገር ግን ትፀንሻለሽ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች