Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 17:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 የቍልፈታችሁንም ሥጋ ትገረዛላችሁ፥ በእኔና በእናንተ መካከል ላለውም ቃል ኪዳን ምልክት ይሆናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ስለዚህ ሁላችሁም ሸለፈታችሁን ትገረዛላችሁ፤ ይህም በእኔና በእናንተ መካከል ላለው ኪዳን ምልክት ይሆናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ሸለፈታችሁን ትገረዛላችሁ፤ ይህም በእኔና በእናንተ መካከል ላለው ቃል ኪዳን ምልክት ይሆናል፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 የሰ​ው​ነ​ታ​ች​ሁን ቍል​ፈት ትገ​ረ​ዛ​ላ​ችሁ፤ በእ​ኔና በእ​ና​ንተ መካ​ከል ላለ​ውም ቃል ኪዳን ምል​ክት ይሆ​ናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 የቍልፈታችሁንም ሥጋ ትገረዛላችሁ፤ በእኔና በእናንተ መካከል ላለውም ቃል ኪዳን ምልክት ይሆንል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 17:11
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሳይገረዝም በእምነቱ ባገኘው የጽድቅ ማኅተም፥ መገረዝን እንደ ምልክት ተቀበለ፤ ሳይገረዙ ለሚያምኑ ሁሉ፥ ለእነርሱም ጽድቅ ሆኖ እንዲቆጠርላቸው አባት ነውና፤


የመገረዝንም ኪዳን ሰጠው፤ እንዲሁም ይስሐቅን ወለደ፤ በስምንተኛውም ቀን ገረዘው፤ ይስሐቅም ያዕቆብን ያዕቆብም ዐሥራ ሁለቱን የአባቶችን አለቆች።


እንግዲህ እናንተ የልባችሁን ሸለፈት ግረዙ፥ ከእንግዲህ ወዲህም አንገተ ደንዳና አትሁኑ።


ከዚያም ዳዊት፥ “የመቶ ፍልስጥኤማውያን ሸለፈት ማጫ የከፈልሁባትን ሚስቴን ሜልኮልን ስጠኝ” ብሎ ወደ ሳኦል ልጅ ወደ ኢያቡስቴ መልክተኞች ላከበት።


ኢያሱም የባልጩት መቁረጫ ሠርቶ የግርዛት ኮረብታ በተባለ ስፍራ የእስራኤልን ልጆች ገረዘ።


እንግዳ ሰውም በመካከላችሁ ቢቀመጥ ለጌታም ፋሲካን ሊያደርግ ቢፈልግ፥ እርሱና የእርሱ ወንዶች ሁሉ ይገረዙ ከዚያም ይቅረብ ያድርግም፤ እንደ አገሩ ተወላጅም ይሆናል፤ ያልተገረዘ ሁሉ ግን ከእርሱ አይብላ።


ፂፖራም ባልጩት ወሰደች፥ የልጇንም ሸለፈት ገረዘች፥ እግሩንም ነክታ፦ “አንተ ለእኔ የደም ሙሽራ ነህ” አለች።


እንዲህም ሲል እግዚአብሔር ተናገረ፦ “በእኔና በእናንተ፥ ከእናንተም ጋር ባለው በሕያው ፍጥረት ሁሉ መካከል፥ ለዘለዓለም የማደርገው፥ የቃል ኪዳን ምልክት ይህ ነው፥


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች