ዘፍጥረት 16:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)2 ሦራም አብራምን፦ እነሆ፥ እንዳልወልድ እግዚአብሔር ዘጋኝ፥ ምናልባት ከእርሷ በልጅ እታነጽ እንደሆነ ወደ እርሷ ግባ አለችው። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም2 አብራምንም፣ “እግዚአብሔር ልጅ እንዳልወልድ አድርጎኛል። ምናልባት በርሷ በኩል ልጆች አገኝ እንደሆን ሄደህ ከአገልጋዬ ጋራ ተኛ” አለችው። አብራምም ሦራ ባለችው ተስማማ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም2 ስለዚህ ሣራይ አብራምን “እነሆ፥ እግዚአብሔር ልጅ እንዳልወልድ ከልክሎኛል፤ ወደዚህች ወደ አገልጋዬ ግባ፤ ምናልባት በእርስዋ በኩል ልጅ አገኝ ይሆናል” አለችው። አብራምም ሣራይ ባለችው ነገር ተስማማ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)2 ሦራም አብራምን፥ “እነሆ፥ እንዳልወልድ እግዚአብሔር ዘጋኝ፤ ከእርስዋ ትወልድ ዘንድ ወደ አገልጋዬ ሂድ” አለችው። አብራምም የሚስቱን የሦራን ቃል ሰማ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)2 ሦራም አብራምን፤ እነሆ እንዳልወልድ እግዚአብሔር ዘጋኝ ምናልባት ከእርስዋ በልጅ እታነጽ እንደ ሆነ ወደ እርስዋግባ አለችው፤ ምዕራፉን ተመልከት |