Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 15:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ደግሞም በባርነት በሚገዙአቸው ሕዝብ ላይ እኔ እፈርዳለሁ፥ ከዚያም በኋላ በብዙ ከብት ይወጣሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ነገር ግን በባርነት የሚገዛቸውን ሕዝብ እቀጣዋለሁ፤ ከዚያም ብዙ ሀብት ይዘው ይወጣሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 በባርነት የሚገዛቸውን ሕዝብ እቀጣለሁ፤ ከዚያም በኋላ ብዙ ሀብት ይዘው ከዚያ አገር ይወጣሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ደግ​ሞም የሚ​ያ​ሠ​ቃ​ዩ​አ​ቸ​ውን እኔ እፈ​ር​ድ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ። ከዚ​ህም በኋላ ከብዙ ገን​ዘብ ጋር ወደ​ዚህ ይወ​ጣሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ደግሞም በባርነት በገዙአቸው ሕዝብ ላይ እኔ እፈርዳለሁ ከዚያም በኍላ በብዙ ከብት ይወጣሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 15:14
24 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ያዕቆብ ወደ ግብጽ ከገባ በኋላ፥ አባቶቻችሁ ጌታ እንዲረዳቸው ወደ እርሱ ጮኹ፤ ጌታም የቀድሞ አባቶቻችሁን ከግብጽ ምድር አውጥተው በዚህ ስፍራ እንዲኖሩ ያደረጉትን ሙሴንና አሮንን ላከላቸው።


ጌታ ለሕዝቡ ይፈርዳልና፥ ባርያዎቹንም ይረዳልና።


እኛንና አባቶቻችንን ከባርነት ቤት ከግብጽ ምድር ያወጣን፥ በዓይናችንም ፊት እነዚያን ታላላቅ ተአምራት ያደረገ፥ በሄድንባትም መንገድ ሁሉ ባለፍንባቸውም አሕዛብ ሁሉ መካከል የጠበቀን፥ እርሱ ጌታ አምላካችን ነውና።


ጌታም በግብጽና በፈርዖን በቤቱም ሁሉ ላይ፥ በዓይናችን እያየን፥ ታላቅና አሰቃቂ፥ ምልክት ተአምራትም አደረገ።


እናንተን ግን ጌታ ወስዶ፥ እንደ ዛሬው ሁሉ የርስቱ ሕዝብ እንድትሆኑለት፥ ከብረት እቶን ከግብጽ አውጥቷችኋል።


ግብጽ ሆይ፥ በመካከልሽ በፈርዖንና በባርያዎቹ ሁሉ ላይ ተኣምራትንና ድንቅን ሰደደ።


ከበደሌ ፈጽሞ እጠበኝ፥ ከኃጢአቴም አንጻኝ፥


ስለዚህ ሂድ፥ ሕዝቤን የእስራኤልን ልጆች ከግብጽ እንድታወጣ ወደ ፈርዖን እልክሃለሁ።”


ለአገልጋዩ ለአብርሃም የነገረውን ቅዱስ ቃሉን አስታውሶአልና።


እስራኤልም ዮሴፍን፦ “እነሆ እኔ እሞታለሁ፥ እግዚአብሔርም ከእናንተ ጋር ይሆናል፥ ወደ አባቶቻችሁም ምድር ይመልሳችኋል፥


ዮሴፍም ወንድሞቹን፦ “እኔ እሞታለሁ፥ እግዚአብሔርም መጎብኘትን ይጎበኛችኋል፥ ከዚህችም ምድር ያወጣችኋል፥ ለአብርሃምና ለይስሐቅ ለያዕቆብም ወደ ማለላቸው ምድር ያደርሳችኋል” አላቸው።


እንዲህም ሆነ እኩለ ሌሊት ላይ ጌታ በግብጽ ምድር ያለውን በኩር ሁሉ፥ በዙፋን ከተቀመጠው ከፈርዖን በኩር ጀምሮ በእስር ቤት እስካሉት እስከ እስረኞች በኩር ድረስ፥ የከብቶችንም በኩር ሁሉ መታ።


ደግሞም እግዚአብሔር ‘እንደ ባርያዎች በሚገዙአቸው ሕዝብ ላይ እኔ እፈርድባቸዋለሁ፤ ከዚህም በኋላ ይወጣሉ፤ በዚህም ስፍራ ያመልኩኛል፤’ አለ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች