Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 12:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 የፈርዖንም አለቆች አዩአት፥ በፈርዖንም ፊት አመሰገኑአት፥ ሴቲቱንም ወደ ፈርዖን ቤት ወሰዱአት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 የፈርዖንም ሹማምት ባዩአት ጊዜ፣ ለፈርዖን አድንቀው ነገሩት፤ ወደ ቤተ መንግሥትም ወሰዷት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 እንዲሁም አንዳንድ የፈርዖን ባለሟሎች ባዩአት ጊዜ ስለ ቁንጅናዋ ለፈርዖን ተናገሩ፤ ስለዚህ ወደ ቤተ መንግሥት ተወሰደች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 የፈ​ር​ዖ​ንም አለ​ቆች አዩ​አት፤ በፈ​ር​ዖ​ንም ፊት አደ​ነ​ቁ​አት፤ ወደ ፈር​ዖን ቤትም ወሰ​ዱ​አት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 የፈርዖንም አለቆች አዩአት በፈርዖንም ፊት አመስመገኑአት ሴቲቱንም ወደ ፈርዖን ቤት ወሰዱአት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 12:15
18 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አብርሃም ሚስቱን ሣራን፦ “እኅቴ ናት” አለ፥ የገራርም ንጉሥ አቢሜሌክ በመልክተኛ ሣራን ወሰዳት።


ጋብቻ በሁሉ ዘንድ ክቡር፥ መኝታውም ንጹሕ ይሁን፤ ሴሰኞችንና አመንዝሮችን ግን እግዚአብሔር ይፈርድባቸዋል።


በዚያም የግብጽ ንጉሥ ፈርዖንን፦ ሰዓቱን የሚያሳልፍ ለፍላፊ ብለው ጠሩት።


አስተዳዳሪ ለሐሰተኛ ነገር ትኩረት ቢሰጥ፥ ከእርሱ በታች ያሉት ሁሉ ዓመፀኞች ይሆናሉ።


ወደ ሰው ሚስት የሚገባም እንዲሁ ነው፥ የሚነካትም ሁሉ ሳይቀጣ አይቀርም።


ጌታንና ኃይሉን ፈልጉ፥ ሁልጊዜ ፊቱን ፈልጉ።


የግብጽ ንጉሥ ይረዳኛል ብለህ አስበህ ከሆነ፥ የተቀጠቀጠ ሸምበቆ እንደሚመረኰዝ ሰው መሆንህ ነው፤ እርሱ ተሰብሮ ስንጣሪው እጅህን ያቆስልሃል፤ እንግዲህ የግብጽ ንጉሥ ለሚተማመኑበት ሁሉ እንዲሁ ነው’ ሲል የአሦር ንጉሠ ነገሥት ይጠይቅሃል።”


ሰሎሞን የግብጽን ንጉሥ ሴት ልጅ በማግባት ከንጉሡ ጋር ወዳጅነት መሠረተ፤ እርሷንም አምጥቶ ቤተ መንግሥቱን፥ የጌታን ቤትና የኢየሩሳሌምን ዙሪያ ቅጽር ሠርቶ እስኪጨርስ ድረስ በዳዊት ከተማ አኖራት።


ፈርዖንም ይህን ነገር በሰማ ጊዜ ሙሴን ሊገድለው ፈለገ። ሙሴ ግን ከፈርዖን ፊት ኮበለለ፥ በምድያምም ምድር ተቀመጠ፥ በውኃም ጉድጓድ አጠገብ ተቀመጠ።


የፈርዖንም ልጅ ልትታጠብ ወደ ወንዝ ወረደች፤ ደንገጥሮችዋም በወንዝ ዳር ይሄዱ ነበር፤ ሣጥኑንም በቄጠማ ውስጥ አየች፥ ደንገጥሩዋንም ልካ አስመጣችው።


ድፍን ሁለት ዓመት ካለፈ በኋላ ፈርዖን ሕልም ዐለመ፤ በሕልሙም፥ በዐባይ ወንዝ ዳር ቆሞ ነበር፤


ፈርዖንም በመጠጥ አሳላፊዎቹ አለቃና በእንጀራ ቤቱ አዛዥ፥ በሁለቱም ሹማምንቱ ላይ ክፉኛ ተቈጣ፤


የሰው ልጅ ሆይ፥ ስለ ግብጽ ንጉሥ ስለ ፈርዖን ሙሾ አውርድ፥ እንዲህም በለው፦ በሕዝቦች መካከል አንበሳ መሰልህ፥ እንደ ባሕር አውሬ ነበርህ፤ በወንዞችህም ገንፍለህ ወጥተሃል፥ ውኃውንም በእግርህ አደፍርሰሃል፥ ወንዞችህንም አሳድፈሃል።


የግብጽንም ንጉሥ ፈርዖንን ባርያዎቹንም አለቆቹንም ሕዝቡንም ሁሉ፥


አብራምም ወደ ግብጽ በገባ ጊዜ የግብጽ ሰዎች ሴቲቱ እጅግ ውብ እንደ ሆነች አዩ፥


የዚያም ስፍራ ሰዎች ስለ ሚስቱ ጠየቁት፥ እርሱም፦ “እኅቴ ናት” አለ፥ የዚያም ስፍራ ስዎች ለርብቃ ሲሉ እንዳይገድሉኝ ብሎ ሚስቴ ናት ማለትን ፈርቶአልና፥ እርሷ ውብ ነበረችና።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች