Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 1:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 እግዚአብሔርም፦ “በውኆች መካከል ጠፈር ይሁን፥ በውኃና በውኃ መካከልም ይክፈል” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 እግዚአብሔር፣ “ውሃን ከውሃ የሚለይ ጠፈር በውሆች መካከል ይሁን” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር “ውሃውን ከውሃ የሚለይ ጠፈር ይሁን” አለ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “በው​ኃው መካ​ከል ጠፈር ይሁን፤ በው​ኃና በውኃ መካ​ከ​ልም ይለይ” አለ፤ እን​ዲ​ሁም ሆነ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 እግዚአብሔርም፤ በዉኖች መካከል ጠፈር ይሁን በዉኂ መካከል ይከፈል አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 1:6
23 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እንደ ቀለጠ መስተዋት ብርቱ የሆኑትን ሰማያት ከእርሱ ጋር ልትዘረጋ ትችላለህን?


ምድርን በኃይሉ የፈጠረ፥ ዓለምን በጥበቡ የመሠረተ፥ ሰማያትንም በማስተዋሉ የዘረጋ እርሱ ነው።


በጌታ ቃል ሰማዮች ጸኑ፥ በአፉም እስትንፋስ ሠራዊታቸው ተፈጠረ፥


ብርሃንን እንደ ልብስ ለበስህ፥ ሰማይንም እንደ ድንኳን መጋረጃ ዘረጋህ፥


እርሱ ተናግሮአልና፥ ሆኑም፥ እርሱ አዘዘ፥ ጸኑም።


ሰማየ ሰማያት፥ አመስግኑት፥ ከሰማያት በላይ ያላችሁም ውኃዎችም እንዲሁ።


ስለ እስራኤል የተነገረ የጌታ ቃል ይህ ነው። ሰማያትን የዘረጋ፥ ምድርንም የመሠረተ፥ የሰውንም መንፈስ በውስጡ የሠራ ጌታ እንዲህ ይላል፦


ለመዘምራን አለቃ፥ የዳዊት መዝሙር።


እግዚአብሔርም አለ፦ “ውኃ ሕያው ነፍስ ያላቸውን ተንቀሳቃሾች ታስገኝ፥ ወፎችም ከምድር በላይ ከሰማይ ጠፈር በታች ይብረሩ።”


በመንፈሱ ሰማያት ውበትን አገኙ፥ እጁም የሚሸሸውን እባብ ወጋች።


ሃሌ ሉያ። ጌታን በመቅደሱ አወድሱት፥ በኃይሉ ጠፈር አወድሱት።


የውኃውንም ሙላት በደመና ላይ ይጭናል፥ የብርሃኑንም ደመና ይበታትናል፥


ደመናት ዝናብ በሞሉ ጊዜ በምድር ላይ ያፈስሱታል፥ ዛፍም ወደ ደቡብ ወይም ወደ ሰሜን ቢወድቅ፥ ዛፉ በወደቀበት ስፍራ በዚያ ይኖራል።


እግዚአብሔርም አለ፦ “ቀንና ሌሊትን ይለዩ ዘንድ ብርሃናት በሰማይ ጠፈር ይሁኑ፥ ለምልክቶች ለዘመኖች ለዕለታት ለዓመታትም ይሁኑ፥


ጌታ ግን እውነተኛ አምላክ ነው፤ እርሱም ሕያው አምላክና የዘለዓለም ንጉሥ ነው፤ ከቁጣው የተነሣ ምድር ትንቀጠቀጣለች፤ አሕዛብም መዓቱን መቋቋም አይችሉም።


እነዚህ ሰዎች ከብዙ ዘመን በፊት ሰማያት በእግዚአብሔር ቃል መፈጠራቸውን ምድርም የተሠራችው ከውሃና በውሃ መሆኑን ሆን ብለው አያስተውሉም።


እርሱ በምድር ክበብ ላይ ይቀምጣል፥ በእርሷም የሚኖሩት እንደ አንበጣ ናቸው፤ ሰማያትን እንደ መጋረጃ የሚዘረጋቸው እንደ ድንኳንም ለመኖርያ የሚዘረጋቸው፥


ሰማያት የእግዚአብሔርን ክብር ይናገራሉ፥ ጠፈርም የእጁን ሥራ ያወራል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች