Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ገላትያ 1:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ለእርሱ ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ክብር ይሁን፤ አሜን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ከዘላለም እስከ ዘላለም ለርሱ ክብር ይሁን። አሜን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ለእግዚአብሔር ክብር ይሁን! አሜን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ለእ​ርሱ ክብር ይሁን፤ ከዘ​ለ​ዓ​ለም እስከ ዘለ​ዓ​ለም አሜን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ለአብ ከዘላለም እስከ ዘላለም ክብር ይሁን፤ አሜን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ገላትያ 1:5
23 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሁሉም ከእርሱ፥ በእርሱና ለእርሱም ነውና፤ ክብር ለዘለዓለም ለእርሱ ይሁን፤ አሜን።


እርሱ ብቻ አዳኛችን ለሆነው አምላክ፥ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ክብር፥ ግርማ፥ ኃይልና ሥልጣን ከዘመናት ሁሉ በፊት፥ አሁንም እስከ ዘለዓለምም ድረስ ይሁን፤ አሜን።


በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በፊቱ ደስ የሚያሰኘውን በእናንተ እያደረገ፥ ፈቃዱን ትፈጽሙ ዘንድ በመልካም ሥራ ሁሉ ፍጹማን ያድርጋችሁ፤ ለእርሱ እስከ ዘላለም ድረስ ክብር ይሁን፤ አሜን።


የምስጋናው ስም ለዓለምና ለዘለዓለም ይባረክ፥ ምስጋናውም ምድርን ሁሉ ይምላ። አሜን፥ አሜን።


በታላቅ ድምፅም “የፍርዱ ሰዓት ደርሶአልና እግዚአብሔርን ፍሩ፤ ክብርንም ስጡት፤ ሰማይንና ምድርንም ባሕርንም የውሃንም ምንጮች ለሠራው ስገዱለት፤” አለ።


“አሜን ውዳሴ፥ ክብር፥ ጥበብ፥ ምስጋና ገናናነት፥ ክብር ኃይልና ብርታት ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ድረስ ለአምላካችን ይሁን! አሜን።” አሉ።


በታላቅም ድምፅ “የታረደው በግ ኃይልና ባለጠግነት ጥበብም ብርታትም ገናናነትም ክብርም ውዳሴም ሊቀበል ይገባዋል” አሉ።


ነገር ግን በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና እውቀት እደጉ። ለእርሱ አሁንም ለዘለዓለምም ክብር ይሁን! አሜን።


ለዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ክብርና ኃይል ለእርሱ ይሁን! አሜን።


ጌታም ከክፉ ነገር ሁሉ ያድነኛል፤ እርሱም ለሰማያዊው መንግሥቱ እንድሆን ይጠብቀኛል፤ ለእርሱ ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ክብር ይሁን፤ አሜን።


ለዘመናትም ንጉሥ፥ ለማይሞተው፥ ለማይታየው፥ ብቻውን አምላክ ለሆነው መፈራትና ክብር ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ይሁን! አሜን።


ለአምላካችንና ለአባታችን ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ድረስ ክብር ይሁን፤ አሜን።


ይኸውም በክርስቶስ አስቀድመን ተስፋ ያደረግን እኛ ደግሞ ለክብሩ ምስጋና እንድንሆን ነው።


እርሱ ብቻ ጥበበኛ ለሆነው አምላክ በኢየሱስ ክርስቶስ ለዘለዓለም ክብር ይሁን፤ አሜን።


“ክብር ለእግዚአብሔር በአርያም ይሁን! ሰላምም ደስ በሚሰኝባቸው ሰዎች መካከል በምድር ይሁን!” አሉ።


ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ አስተምሩአቸው፤ እነሆ እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።”


ከክፉ አድነን እንጂ ወደ ፈተና አታግባን።’


ለጌታ ክብርን ይስጡ፥ ምስጋናውንም በደሴቶች ይናገሩ።


ስለዚህ ጌታን በምሥራቅ፥ የእስራኤልንም አምላክ የጌታንም ስም በባሕር ደሴቶች አክብሩ።


እኔንም ስለ ቅንነቴ ደገፍከኝ፥ በፊትህም ለዘለዓለም አጸናኸኝ።


አሁንም እንግዲህ፥ አምላካችን ሆይ! እንገዛልሃለን፥ ለክቡር ስምህም ምስጋና እናቀርባለን።


ስለዚህ ምግብ ወንድሜን የሚያሰናክለው ከሆነ፥ ወንድሜን ላለማሰናከል ፈጽሞ ሥጋ አልበላም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች