ዕዝራ 8:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)15 ወደ አኅዋ በሚፈሰው ወንዝ ሰበሰብኋቸው፥ በዚያም ሦስት ቀን ሰፈርን፤ ሕዝቡንና ካህናቱን ስመለከት በዚያ ከሌዊ ልጆች ማንንም አላገኘሁም። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም15 እኔም ወደ አኅዋ በሚፈስሰው ወንዝ አጠገብ ሰዎቹን ሰበሰብኋቸው፤ በዚያም ሦስት ቀን ቈየን። ሕዝቡንና ካህናቱን ስመለከት፣ ከሌዊ ወገን የሆነ አንድም ሰው በዚያ አላገኘሁም። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም15 እኔ ዕዝራ ወደ አሀዋ በሚፈሰው ወንዝ አጠገብ መላውን ጉባኤ ሰበሰብኩ፤ በዚያም ሰፍረን ለሦስት ቀኖች ቈየን፤ በዚያም ጉባኤ ውስጥ ከካህናት በቀር ሌዋውያን አለመኖራቸውን ተገነዘብኩ፤ ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)15 ወደ አኅዋም ወደሚፈስስ ወንዝ ሰበሰብኋቸው፤ በዚያም ሦስት ቀን ሰፈርን፤ ሕዝቡንና ካህናቱንም ስቈጥራቸው በዚያ ከሌዊ ልጆች ማንንም አላገኘሁም። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)15 ወደ አኅዋም ወደሚፈስስ ወንዝ ሰበሰብኋቸው፤ በዚያም ሦስት ቀን ሰፈርን፤ ሕዝቡንና ካህናቱን ስቈጥራቸው በዚያ ከሌዊ ልጆች ማንንም አላገኘሁም። ምዕራፉን ተመልከት |