ዕዝራ 7:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)17 ስለዚህ በዚህ ገንዘብ ወይፈኖችን፥ አውራ በጎችንና ጠቦቶችን ከእህል ቁርባኖቻቸውና ከመጠጥ ቁርባኖቻቸው ጋር ተግተህ ግዛ፥ በኢየሩሳሌምም ባለው በአምላካችሁ ቤት መሠዊያ ላይ አቅርባቸው። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም17 በዚህም ገንዘብ ወይፈኖችን፣ አውራ በጎችንና ጠቦቶችን፣ ከእህል ቍርባኖቻቸውና ከመጠጥ ቍርባኖቻቸው ጋራ መግዛት እንዳለብህ አትርሳ፤ እነዚህንም በኢየሩሳሌም በሚገኘው በአምላካችሁ ቤተ መቅደስ መሠዊያ ላይ አቅርብ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም17 ይህም ገንዘብ በጥንቃቄ ሥራ ላይ እንዲውል አድርግ፤ ወይፈኖችን፥ የበግ አውራዎችንና ጠቦቶችን፥ ለመባ የሚሆነውን እህልና የወይን ጠጅ ጭምር በኢየሩሳሌም በተሠራው በአምላክህ ቤተ መቅደስ ውስጥ በሚገኘው መሠዊያ ላይ የሚቀርበውን መባ ሁሉ ግዛበት። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)17 ስለዚህ በዚህ መጽሐፍ ያዘዝሁህ ትእዛዝ ይህ ነው። በዚህ ገንዘብ ወይፈኖችንና አውራ በጎችን፥ ጠቦቶችንም፥ የእህላቸውንና የመጠጣቸውን ቍርባን ተግተህ ግዛ፤ በኢየሩሳሌምም ባለው በአምላካችሁ ቤት መሠዊያ ላይ አቅርባቸው። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)17 ስለዚህ በዚህ ገንዘብ ወይፈኖችንና፥ አውራ በጎችን፥ ጠቦቶችንም፥ የእህላቸውንና የመጠጣቸውን ቍርባን ተግተህ ግዛ፤ በኢየሩሳሌምም ባለው በአምላካችሁ ቤት መሠዊያ ላይ አቅርባቸው። ምዕራፉን ተመልከት |