ዕዝራ 6:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)4 በሦስት መደዳ ታላላቅ ድንጋይ፥ አንድ መደዳ እንጨት ይደረግ፤ ወጪውም ከንጉሡ ቤት ይሰጥ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም4 በሦስት ዙር ታላላቅ ድንጋዮችና በአንድ ዙር ዕንጨት ይሠራ፤ ወጪውም ከቤተ መንግሥቱ ግምጃ ቤት ይከፈል። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም4 ቅጽሮቹም ከድንጋይ በተሠሩት በሦስቱም ዙር ግንቦች አናት ላይ አንዳንድ ዙር ከእንጨት የተሠራ ድምድማት ይኑራቸው፤ ለዚህም ሁሉ ሥራ የሚያስፈልገው ገንዘብ ከቤተ መንግሥቱ ግምጃ ቤት ወጪ ሆኖ ይሰጥ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)4 በሦስት ተራ ታላላቅ ድንጋይ፥ በአንድ ተራ እንጨት ይደረግ፤ ወጭውም ከንጉሡ ቤት ይሰጥ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)4 በሦስት ተራ ታላላቅ ድንጋይ፥ በአንድ ተራ እንጨት ይደረግ፤ ወጪውም ከንጉሡ ቤት ይሰጥ። ምዕራፉን ተመልከት |