ዕዝራ 6:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)3 በንጉሡ በቂሮስ በመጀመሪያው ዓመት ንጉሡ ቂሮስ በኢየሩሳሌም ስላለው ስለ እግዚአብሔር ቤት እንዲህ ብሎ አዘዘ፥ መሥዋዕት የሚሠዋበት ቦታ፥ ይህ ቤት ይሠራ፥ በጽኑም ይመሥረት፤ ርዝመቱ ስድሳ ክንድ ስፋቱም ስድሳ ክንድ ይሁን። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም3 በንጉሥ ቂሮስ የመጀመሪያው ዓመት በኢየሩሳሌም ስለሚገኘው የአምላክ ቤተ መቅደስ ንጉሡ የሰጠው ትእዛዝ ይህ ነው፤ ቤተ መቅደሱ መሥዋዕት የሚቀርብበት ቦታ ሆኖ እንደ ገና ይሠራ፤ መሠረቱም ይጣል፤ ቁመቱ ስድሳ ክንድ፣ ወርዱም ስድሳ ክንድ ይሁን፤ ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም3 “ቂሮስ ንጉሠ ነገሥት በሆነ በመጀመሪያው ዓመት በኢየሩሳሌም የነበረው ቤተ መቅደስ የሚቃጠለውና ሌላውም ልዩ ልዩ መሥዋዕት ይቀርብበት ዘንድ እንደገና እንዲሠራ በመፍቀድ ትእዛዝ ሰጥቶአል፤ የቤተ መቅደሱም ርዝመት ኻያ ሰባት ሜትር፥ ስፋቱም ኻያ ሰባት ሜትር መሆን አለበት። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)3 በንጉሡ በቂሮስ በመጀመሪያው ዓመት ንጉሡ ቂሮስ በኢየሩሳሌም ስላለው የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንዲህ ብሎ አዘዘ፥ “ይህ ቤት ይሠራ መሥዋዕት የሚቀርብበትም ቦታ ይሠራ፤ ቁመቱም ስድሳ ክንድ፥ ወርዱም ስድሳ ክንድ ይሁን። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)3 በንጉሡ በቂሮስ በመጀመሪያው ዓመት ንጉሡ ቂሮስ እንዲህ ብሎ አዘዘ፤ በኢየሩሳሌም ያለው የእግዚአብሔር ቤት፥ መሥዋዕት የሚቀርብበት ቦታ፥ ይህ ቤት ይሠራ፤ በጽኑም ይመሥረት፤ ቁመቱ ስድሳ፥ ክንድ ወርዱም ስድሳ ክንድ ይሁን። ምዕራፉን ተመልከት |