ዕዝራ 6:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)11 ይህንም ትእዛዝ የሚያደናቅፍ ሁሉ፥ ምሰሶ ከቤቱ ተነቅሎ እርሱ ይሰካበት፥ ቤቱም የጉድፍ መጣያ ይሁን ብዬ አዝዣለሁ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም11 ደግሞም ይህን ትእዛዝ የሚለውጥ ማንም ሰው ቢኖር፣ ከቤቱ ምሰሶ ተነቅሎ በምሰሶው ላይ እንዲሰቀል፣ ስለ ወንጀሉም ቤቱ የቈሻሻ መጣያ እንዲሆን አዝዣለሁ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም11 ከዚህም ሌላ ማስታወቅ የምፈልገው ነገር ይህን መመሪያ የማይቀበልና የማይታዘዝ ማንም ሰው ቢኖር ከቤቱ የእንጨት ምሰሶዎች አንዱ ተነቅሎ በአንዱ ጫፍ በኩል እንዲሾል ከተደረገ በኋላ በሰውነቱ ላይ ይሰካበት፤ ቤቱም ፈራርሶ የጉድፍ መጣያ ይሁን። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)11 ይህንም ትእዛዝ የሚለውጥ ሁሉ ምሰሶው ከቤቱ ተነቅሎ እርሱ ይሰቀልበት፤ በላዩም ይገደል፤ ቤቱም የጕድፍ መጣያ ይደረግ ብዬ አዝዣለሁ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)11 ይህንም ትእዛዝ የሚለውጥ ሁሉ፥ ምሰሶው ከቤቱ ተነቅሎ እርሱ ይሰቀልበት፤ ቤቱም የጉድፍ መጣያ ይደረግ ብዬ አዝዣለሁ። ምዕራፉን ተመልከት |