ዕዝራ 5:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)8 ወደ ይሁዳ አገር ወደ ታላቁ አምላክ ቤትም እንደ ሄድን በንጉሡ ዘንድ ይታወቅ፥ እርሱም በትልቅ ድንጋይ ተሠራ፥ በቅጥሩም ውስጥ እንጨት ተደረገ፥ ያም ሥራ በጥንቃቄ ይሠራል፥ በእጃቸውም ይከናወናል። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም8 የታላቁ አምላክ ቤተ መቅደስ ወደሚገኝበት ወደ ይሁዳ አውራጃ ሄደን እንደ ነበር በንጉሡ ዘንድ የታወቀ ይሁን። ሕዝቡ ቤተ መቅደሱን በታላላቅ ድንጋዮች እየገነቡና ቅጥሩንም በወፍራም ምሰሶዎች እየሠሩ ነው፤ ሥራው በትጋት በመከናወንና በእነርሱም አመራር በመፋጠን ላይ ይገኛል። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም8 ወደ ይሁዳ ምድር ሄደን የታላቁ አምላክ ቤተ መቅደስ በድንጋይና በጠርብ እንጨት ሲሠራ ማየታችን ለግርማዊነትዎ የታወቀ ይሁን፤ ሥራውም በሽማግሌዎቹ መሪነት በጥንቃቄና በፍጥነት እየተሠራ ነው። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)8 ወደ ይሁዳ ሀገር ወደ ታላቁም አምላክ ቤት እንደ ሄድን ንጉሡ ይወቅ፤ እርሱም በጥሩ ድንጋይ ይሠራል፤ በቅጥሩም ውስጥ ልዩ እንጨት ይደረጋል፤ ያም ሥራ በትጋት ይሠራል፤ በእጃቸውም ይከናወናል። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)8 ወደ ይሁዳ አገር ወደ ታላቁም አምላክ ቤት እንደ ሄድን ንጉሡ ይወቅ፤ እርሱም በትልቅ ድንጋይ ተሠራ፤ በቅጥሩም ውስጥ እንጨት ተደረገ፤ ያም ሥራ በትጋት ይሠራል፤ በእጃቸውም ይከናወናል። ምዕራፉን ተመልከት |