ዕዝራ 5:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)14 ናቡከደነፆር በኢየሩሳሌም ከነበረው መቅደስ የወሰደውን፥ ወደ ባቢሎንም መቅደስ ያመጣውን የእግዚአብሔርን ቤት የወርቅንና የብርን ዕቃዎች ንጉሡ ቂሮስ ከባቢሎን መቅደስ አውጥቶ ሼሽባጻር ለተባለው፥ ገዢ ላደረገው ሰጠው፤ ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም14 ናቡከደነፆር ከኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ አውጥቶ ባቢሎን በሚገኘው ቤተ መቅደስ ውስጥ ያኖራቸውን የእግዚአብሔርን ቤት የወርቅና የብር ዕቃዎች ከባቢሎን ቤተ መቅደስ አስመጣ። ከዚያም ንጉሥ ቂሮስ፣ አገረ ገዥ አድርጎ ለሾመውና ሰሳብሳር ተብሎ ለሚጠራው ሰው ሰጠው፤ ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም14 ናቡከደነፆር በዚሁ በኢየሩሳሌም ተሠርቶ ከነበረው ከቀድሞው ቤተ መቅደስ ማርኮ የወሰዳቸውንና በባቢሎን ማምለኪያ ስፍራው ውስጥ ያኖራቸውን ከወርቅና ከብር የተሠሩ ንዋያተ ቅድሳትም ሁሉ ቂሮስ መልሶ አስረክቦናል፤ ንዋያተ ቅድሳቱንም ያስረከበን የይሁዳ ገዢ አድርጎ በሾመው ሼሽባጻር ተብሎ በሚጠራው ሰው አማካይነት ነው። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)14 ናቡከደነፆርም በኢየሩሳሌም ከነበረው መቅደስ የወሰደውን፥ ወደ ባቢሎንም መቅደስ ያፈለሰውን የእግዚአብሔርን ቤት የወርቁንና የብሩን ዕቃ ንጉሡ ቂሮስ ከባቢሎን መቅደስ አውጥቶ ለቤተ መዛግብቱ ሹም ለሲሳብሳር ሰጠውና፦ ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)14 ናቡከደነፆርም በኢየሩሳሌም ከነበረው መቅደስ የወሰደውን፥ ወደ ባቢሎንም መቅደስ ያፈለሰውን የእግዚአብሔርን ቤት የወርቅንና የብርን ዕቃ ንጉሡ ቂሮስ ከባቢሎን መቅደስ አውጥቶ ሰሳብሳር ለተባለው ለሹሙ ሰጠውና፦ ምዕራፉን ተመልከት |