ዕዝራ 4:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)13 አሁንም ይህች ከተማ ከተገነባች፥ የቅጥሮቿም ሥራ ከተጠናቀቀ፥ ግብርና ቀረጥ መጥንም እንዳይሰጡ፥ ንጉሡንም እንደሚጎዳ በንጉሡ ዘንድ የታወቀ ይሁን። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም13 ከዚህም በላይ ይህች ከተማ ከተሠራች፣ ቅጥሮቿም እንደ ገና ከተገነቡ፣ ቀረጥና እጅ መንሻ ወይም ግብር እንደማይከፍሉ፣ የቤተ መንግሥቱም ገቢ እንደሚቀንስ በንጉሡ ዘንድ የታወቀ ይሁን። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም13 ስለዚህም ንጉሥ ሆይ! ይህች ከተማ እንደገና ከተሠራችና የቅጽሮችዋም ሥራ ከተጠናቀቀ፥ ሕዝቡ ግብር መክፈላቸውን ያቆማሉ፤ ለግርማዊነትዎ የሚቀርበውም የንጉሣዊ ቤተ መንግሥት ገቢ ሊቀነስ የሚችል መሆኑን ይታወቅ፤ ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)13 አሁንም ይህች ከተማ የተሠራች እንደ ሆነ፥ ቅጥርዋም የታደሰ እንደ ሆነ፥ ግብርና ቀረጥ መጥንም እንደማይሰጡ፥ ንጉሡ ይወቅ፤ ይህም መንግሥትን ይጐዳል። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)13 አሁንም ይህች ከተማ የተሠራች እንደ ሆነ፥ ቅጥርዋም የታደሰ እንደ ሆነ፥ ግብርና ቀረጥ መጥንም እንዳይሰጡ፥ የንጉሡም ገቢው እንዲጐድል ንጉሡ ይወቅ። ምዕራፉን ተመልከት |