ዕዝራ 3:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)13 ሕዝቡ ግን ደስ ብሎአቸው የሚጮኹትን ድምፅ ከሕዝቡ ልቅሶ ድምፅ መለየት አልቻለም፤ ሕዝቡም በታላቅ ድምፅ እልል ይሉ ነበር፥ ድምፁም ከሩቅ ይሰማ ነበር። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም13 የሕዝቡ ጩኸት ድብልቅልቅ ያለ ስለ ነበር፣ የደስታውን እልልታ ከልቅሶው ጩኸት መለየት የሚችል ማንም አልነበረም፤ ድምፁም ከሩቅ ይሰማ ነበር። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም13 የሚያሰሙት ከፍተኛ ድምፅ በስፋት እስከ ሩቅ ያስተጋባ ስለ ነበር ማንም ሰው የደስታውን እልልታና የለቅሶውን ጩኸት ድምፅ ለመለየት አልተቻለውም። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)13 ደስ ብሎአቸው የሚጮኹትን ድምፅ ከሕዝቡ ልቅሶ ድምፅ መለየት የሚችል አልነበረም፥ ሕዝቡ በታላቅ ድምፅ ይጮኽ ነበርና ድምፁም ከሩቅ ይሰማ ነበርና። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)13 ደስ ብሎአቸው የሚጮኹትን ድምፅ ከሕዝቡ ልቅሶ ድምፅ መለየት የሚችል አልነበረም፤ ሕዝቡም በታላቅ ድምፅ ይጮኽ ነበር፤ ድምፁም ከሩቅ ይሰማ ነበር። ምዕራፉን ተመልከት |