ዕዝራ 3:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)12 የመጀመሪያውን ቤት ያዩ ብዙ ካህናት፥ ሌዋውያን፥ የአባቶች አለቆችና ሽማግሌዎች ግን ይህ ቤት በፊታቸው በተመሠረተ ጊዜ በታላቅ ድምፅ ያለቅሱ ነበር፥ ብዙ ሰዎችም በደስታ እልል ይሉ ነበር፤ ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም12 የቀድሞውን ቤተ መቅደስ ያዩ በዕድሜ የሸመገሉ ብዙ ካህናት፣ ሌዋውያንና የቤተ ሰብ አለቆች የዚህ ቤተ መቅደስ መሠረት ሲጣል ባዩ ጊዜ፣ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው አለቀሱ፤ ሌሎቹ ግን የደስታ ጩኸት አሰሙ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም12 ከሽማግሌዎቹ ካህናትና ሌዋውያን ብዙዎቹ እንዲሁም የጐሣ መሪዎች የቀድሞውን ቤተ መቅደስ አሠራር በዐይናቸው አይተው ስለ ነበር የዚህኛውን ቤተ መቅደስ መሠረት ሲጣል ባዩ ጊዜ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው አለቀሱ፤ በዚያ የነበሩት የሌሎቹ እልልታ ግን አስተጋባ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)12 የፊተኛውን ቤት ያዩ ሽማግሌዎች የሆኑ ብዙ ካህናትና ሌዋውያን፥ የአባቶችም ቤቶች አለቆች ግን ይህ መቅደስ በፊታቸው በተመሠረተ ጊዜ በታላቅ ድምፅ ያለቅሱ ነበር፤ ብዙ ሰዎችም እየዘመሩ በደስታ ይጮኹ ነበር፤ ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)12 የፊተኛውን ቤት ያዩ ሽማግሌዎች የሆኑ ብዙ ካህናትና ሌዋውያን፥ የአባቶችም ቤቶች አለቆች ግን ይህ መቅደስ በፊታቸው በተመሠረተ ጊዜ በታላቅ ድምፅ ያለቅሱ ነበር፤ ብዙ ሰዎችም በደስታ ይጮኹ ነበር፤ ምዕራፉን ተመልከት |