Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዕዝራ 2:70 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

70 ካህናቱ፥ ሌዋውያኑ፥ ከሕዝቡም አንዳንዶች፥ መዘምራኑ፥ በር ጠባቂዎቹና፥ የቤተ መቅደስ አገልጋዮቹ፥ በከተሞቻቸው፥ እስራኤልም ሁሉ በከተሞቻቸው ተቀመጡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

70 ካህናቱ፣ ሌዋውያኑ፣ መዘምራኑ፣ በር ጠባቂዎቹና የቤተ መቅደሱ አገልጋዮች፣ ከሌሎች ሰዎች ጋራ በየራሳቸው ከተሞች ሰፈሩ፤ የቀሩት እስራኤላውያንም በየራሳቸው ከተሞች ሰፈሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

70 ካህናቱ፥ ሌዋውያኑና ከሕዝቡም አንዳንዱ በኢየሩሳሌም ወይም በአቅራቢያዋ ሰፈሩ፤ መዘምራኑ፥ የቤተ መቅደስ ዘብ ጠባቂዎችና ለቤተ መቅደሱ ሕንጻ የተመደቡት ሠራተኞች በየአቅራቢያው በሚገኙት ከተሞች ሰፈሩ፤ እንዲሁም የቀሩት እስራኤላውያን የቀድሞ አባቶቻቸው በነበሩባቸው ከተሞች ሰፈሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

70 ካህ​ና​ቱና ሌዋ​ው​ያ​ኑም፥ ከሕ​ዝ​ቡም አያ​ሌ​ዎች፥ መዘ​ም​ራ​ኑና በረ​ኞ​ቹም፥ ናታ​ኒ​ምም በከ​ተ​ሞ​ቻ​ቸው፥ እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ በከ​ተ​ሞ​ቻ​ቸው ተቀ​መጡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

70 ካህናቱና ሌዋውያኑ፥ ከሕዝቡም አያሌዎች፥ መዘምራኑና በረኞቹ፥ ናታኒምም በከተሞቻቸው፥ እስራኤልም ሁሉ በከተሞቻቸው ተቀመጡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዕዝራ 2:70
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከዚያም በኋላ ከሶርያውያን ሰፈር በመነሣት ወደ ሰማርያ ተመልሰው ሄዱ፤ እዚያም እንደ ደረሱ የከተማይቱን ቅጽር በር ዘበኞች ጠርተው “ወደ ሶርያውያን ሰፈር ሄደን ነበር፤ ነገር ግን ምንም ያየነው ሰው ወይም የሰማነው ድምፅ እንኳ የለም፤ ፈረሶችና አህዮች እንደ ታሰሩ ናቸው፤ ድንኳኖቹም ሶርያውያን ትተዋቸው ስለ ሄዱ ባዶአቸውን ናቸው” ሲሉ ነገሩአቸው።


አስቀድሞ ሳኦል ንጉሥ ሆኖ ሳለ እስራኤልን የምታወጣና የምታገባ አንተ ነበርህ፤ ጌታ አምላክህም፦ ‘ሕዝቤን እስራኤልን አንተ ትጠብቃለህ፤ በሕዝቤም በእስራኤል ላይ አለቃ ትሆናለህ’ ብሎህ ነበር።”


በአውራጃዎቻቸውና በከተሞቻቸው መጀመሪያ የተቀመጡ እስራኤልና ካህናት ሌዋውያንም የቤተ መቅደሱም አገልጋዮች ነበሩ።


የባቢሎንም ንጉሥ ናቡከደነፆር ወደ ባቢሎን ከማረካቸው ምርኮኞች ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ ይሁዳ ወደየከተማቸው የተመለሱት የአገር ልጆች እነዚህ ናቸው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች