ሕዝቅኤል 7:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)13 በሕይወት እስካሉ ድረስ ሻጭ ወደሸጠው ነገር አይመለስ፥ ስለ ብዙዎቹ የተነገረው ራእይ አይመለስምና፥ ማንም ሰው በኃጢአቱ ሕይወቱን ማዳን አይችልም። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም13 ሁለቱ በሕይወት እስካሉ ድረስ ሻጩ የሸጠውን መሬት አያስመልስም፤ ስለ መላው ሕዝብ የተነገረው ራእይ አይለወጥምና። ከኀጢአታቸው የተነሣ ሕይወቱን ማትረፍ የሚችል አንድም አይገኝም። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም13 ሻጭና ገዢ በሕይወት እስካሉ ድረስ ሻጭ የሸጠውን ዕቃ መልሶ ሊያገኘው እንደማይችል ሁሉ እንዲሁም ራእዩ የተነገረው ስለ ሁሉም ስለ ሆነ ሊታጠፍ አይችልም። እነርሱም ስለ በበደሉ ሕይወታቸውን ማዳን አይችሉም። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)13 የገዛው ወደ ሻጩ አይመለስም፤ ዳግመኛም በሕይወት ይኖራል፤ ሁለንተናዋን አይቶአልና አልተመለሰም፤ የሰው ሕይወቱ በዐይኑ ፊት ነው። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)13 የሚሸጥም ወደሸጠው ነገር አይመለስም፥ ሰውም በነፍሱ ኃጢአት አይጸናም። ምዕራፉን ተመልከት |