ሕዝቅኤል 32:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)4 በምድር ላይ እተውሃለሁ፥ ለጥ ባለ ሜዳም እጥልሃለሁ፥ የሰማይ ወፎች ሁሉ በአንተ ላይ እንዲኖሩ አደርጋለሁ፥ የምድርን አራዊት ሁሉ ከአንተ አጠግባቸዋለሁ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም4 በምድር ላይ እጥልሃለሁ፤ ሜዳም ላይ እዘረጋሃለሁ፤ የሰማይ ወፎች ሁሉ እንዲሰፍሩብህ አደርጋለሁ፤ የምድር አራዊት ሁሉ በመስገብገብ ይበሉሃል። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም4 በትቢያም ላይ እጥልሃለሁ፤ ሥጋህንም እንዲመገቡት የሰማይ ወፎችና የምድር አራዊትን ሁሉ እጠራለሁ፤ ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)4 በሰፊ ምድረ በዳም እጥልሃለሁ፤ የሰማይንም ወፎች ሁሉ አሳርፍብሃለሁ፤ የምድርንም አራዊት ሁሉ ከአንተ አጠግባቸዋለሁ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)4 በምድርም ላይ እተውሃለሁ፥ በምድረ በዳም ፊት እጥልሃለሁ፥ የሰማይንም ወፎች ሁሉ አሳርፍብሃለሁ፥ የምድርንም አራዊት ሁሉ ከአንተ አጠግባቸዋለሁ። ምዕራፉን ተመልከት |