ሕዝቅኤል 22:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)3 እንዲህም በላት፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በመካከልዋ ደምን የምታፈስ ከተማ ሆይ!ጊዜዋ ደርሶአል፥ እንድትረክስም በራስዋ ላይ ጣዖታትን የምታደርግ፤ ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም3 እንዲህም በላት፤ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ በመካከልሽ ደምን በማፍሰስና ጣዖታትን በመሥራት ራስሽን የምታረክሺ፣ ፍርድንም በራስሽ ላይ የምታፈጥኚ ከተማ ሆይ፤ ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም3 ለከተማይቱ እኔ ልዑል እግዚአብሔር የምለው ይህ ነው፦ በውስጥሽ ያሉትን ብዙዎችን ስለ ገደልሽና ጣዖቶችን በማምለክ ራስሽን ስላረከስሽ እንድትጠፊ የተወሰነበት ጊዜ ተቃርቦአል። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)3 እንዲህም በላት፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጊዜሽ እንዲደርስ በመካከልሽ ደምን የምታፈስሺ፥ እንድትረክሺም በራስሽ ላይ ጣዖታትን የምታደርጊ ከተማ ሆይ! ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)3 እንዲህም በል፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጊዜሽ እንዲደርስ በመካከልሽ ደምን የምታፈስሺ እንዲትረክሺም በራስሽ ላይ ጣዖታትን የምታደርጊ ከተማ ሆይ! ምዕራፉን ተመልከት |