Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሕዝቅኤል 10:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ከኪሩቤል መካከል አንድ ኪሩብ እጁን በኪሩቤል መካከል ወዳለው እሳት ዘርግቶ ከዚያ ወሰደ፥ በፍታ በለበሰው ሰው እጅም አኖረው፥ እርሱም ይዞ ወጣ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ከኪሩቤልም አንዱ በመካከላቸው ወዳለው እሳት እጁን ዘርግቶ ጥቂት ወሰደ፤ በፍታ በለበሰው ሰው እጅ ላይ አኖረው፤ እርሱም ይዞ ወጣ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ከኪሩቤልም አንዱ በመካከላቸው ባለው እሳት ውስጥ እጁን ሰድዶ ጥቂት ፍሞች አነሣና በፍታ በለበሰው ሰው እጅ ላይ አኖረው፤ ሰውየውም ፍሙን ይዞ ሄደ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ከኪ​ሩ​ቤል መካ​ከ​ልም አንዱ ኪሩብ እጁን በኪ​ሩ​ቤል መካ​ከል ወደ አለው እሳት ዘር​ግቶ ከዚያ እሳት ወሰደ፤ የተ​ቀ​ደሰ በፍ​ታም በለ​በ​ሰው ሰው እጅ አኖ​ረው፤ እር​ሱም ይዞ ወጣ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ኪሩብም ከኪሩቤል መካከል እጁን በኪሩቤል መካከል ወዳለው እሳት ዘርግቶ ከዚያ ወሰደ፥ በፍታም በለበሰው ሰው እጅ አኖረው፥ እርሱም ይዞ ወጣ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሕዝቅኤል 10:7
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የሕያዋኑም መልክ የሚነድድ የእሳት ፍም ይመስል ነበር፥ በሕያዋኑም መካከል የሚነድድ ችቦ የሚመስል ወዲህና ወዲያ ይዘዋወር ነበር፥ እሳቱም ብርሃን ነበረው፥ ከእሳቱም መብረቅ ይወጣ ነበር።


በፍታ የለበሰውን ሰው ሲያዘው፦ ከኪሩቤል መካከል ከመንኰራኵሮች መካከል እሳት ውሰድ አለው፥ እርሱም ገብቶ በአንድ መንኰራኵር አጠገብ ቆመ።


ኪሩቤልም ከክንፎቻቸው በታች የሰው እጅ የሚመስል ታየ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች