Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘፀአት 8:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ጌታም እንዲሁ አደረገ፤ በፈርዖን ቤት፥ በአገልጋዮቹም ቤቶች ውስጥ ብዙ የዝንብ መንጋ መጣ፤ በግብጽም ምድር ሁሉ ላይ፤ ከዝንቡ መንጋ የተነሣ ምድር ተበላሸች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “በጧት ተነሥተህ ፈርዖን ወደ ውሃ በሚወርድበት ጊዜ ከፊቱ ቀርበህ እንዲህ በለው፤ ‘እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፤ ያመልኩኝ ዘንድ ሕዝቤን ልቀቅ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ነገ ጠዋት በማለዳ ወደ ንጉሡ ሄደህ ወደ ወንዝ ሲወርድ አግኘው፤ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ብለህ ንገረው፤ ‘ያገለግለኝ ዘንድ ሕዝቤን ልቀቅ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “ማል​ደህ ተነሣ፤ በፈ​ር​ዖ​ንም ፊት ቁም፤ እነሆ፥ እርሱ ወደ ውኃ ይወ​ር​ዳል፤ እን​ዲ​ህም በለው፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በም​ድረ በዳ እን​ዲ​ያ​መ​ል​ኩኝ ሕዝ​ቤን ልቀቅ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፤ “ማልደህ ተነሣ፤ በፈርዖንም ፊት ቁም፤ እነሆ እርሱ ወደ ውኃ ይወርዳል፤ እንዲህም በለው፤ ‘እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፀአት 8:20
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ተናገረ፥ የዝንብ መንጋና ተናካሽ ትንኞች በዳርቻቸው መጡ።


ዝንቦችንም በላያቸው ሰደደባቸው፥ በሉአቸውም፥ በጓጉንቸርም አጠፋቸው።


የፈርዖንም ልጅ ልትታጠብ ወደ ወንዝ ወረደች፤ ደንገጥሮችዋም በወንዝ ዳር ይሄዱ ነበር፤ ሣጥኑንም በቄጠማ ውስጥ አየች፥ ደንገጥሩዋንም ልካ አስመጣችው።


እነርሱም ቃልህን ይሰማሉ፤ አንተና የእስራኤል ሽማግሌዎች ወደ ግብጽ ንጉሥ ትሄዳላችሁ፦ ‘የዕብራውያን አምላክ ጌታ ተገለጠልን፤ ስለዚህ ለአምላካችን ለጌታ እንድንሠዋ የሦስት ቀን መንገድ በምድረ በዳ እንሂድ’ ትሉታላችሁ።


እንዲያገለግለኝ ልጄን ልቀቅ አልሁህ፤ አንተም ትለቅቀው ዘንድ እንቢ አልህ፤ እነሆ እኔ የበኩር ልጅህን እገድላለሁ።’”


ከዚህም በኋላ ሙሴና አሮን ሄደው ፈርዖንን እንዲህ አሉት፦ “የእስራኤል አምላክ ጌታ እንዲህ ይላል፦ ‘በምድረ በዳ በዓል እንዲያደርግልኝ ሕዝቤን ልቀቅ።’”


እነርሱም፦ “የዕብራውያን አምላክ ተገናኘን፤ የሦስት ቀን መንገድ በምድረ በዳ እንድንሄድ፥ ለጌታ ለአምላካችን እንድንሠዋ እንለምንሃለን ካልሆነ ተላላፊ በሽታ ወይም ሰይፍ እንዳይጥልብን” አሉት።


ወደ ፈርዖን በጠዋት ሂድ፤ እነሆ ወደ ውኃ ይወጣል፥ አንተም እንድትገናኘው በወንዝ ዳር ትቆማለህ፤ ወደ እባብም የተለወጠውን በትር በእጅህ ትወስዳለህ።


ጌታም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “አሮንን ‘በትርህን ይዘህ እጅህን በፈሳሾቹ በወንዞቹና በኩሬዎቹ ላይ እጅህን ዘርጋ፥ በግብጽም ምድር ላይ እንቁራሪቶችን አውጣ’ በለው።”


ፈርዖንም ሙሴንና አሮንን ጠርቶ፦ “ሂዱ፥ በምድሪቱ ውስጥ ለአምላካችሁ ሠዉ” አላቸው።


ጌታም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ማልደህ ተነሣ፥ በፈርዖንም ፊት ቁም እንዲህም በለው፦ የዕብራውያን አምላክ ጌታ እንዲህ ይላል፦ ‘እንዲያገለግሉኝ ሕዝቤን ልቀቅ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች