Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘፀአት 8:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 በዚያን ቀን በምድር መካከል እኔ ጌታ እንደሆንሁ እንድታውቅ፥ የዝንብ መንጋ በእርሷ ላይ እንዳይሆን፥ ሕዝቤ የሚቀመጥባትን የጎሼንን ምድር እለያለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ነገር ግን አስማተኞቹ በድብቅ ጥበባቸው ተናካሽ ትንኞችን ለመፍጠር ሲሞክሩ አልቻሉም። ተናካሽ ትንኞቹም ከሰውና ከእንስሳው ላይ አልወረዱም ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 አስማተኞቹ በአስማታቸው ተጠቅመው ተናካሽ ትንኝ እንዲፈላ ለማድረግ ሞከሩ፤ ነገር ግን አልተሳካላቸውም፤ ተናካሽ ትንኝም በሰዎችና በእንስሶች ላይ ተሠራጨ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 የግ​ብፅ ጠን​ቋ​ዮ​ችም በአ​ስ​ማ​ታ​ቸው ቅማል ያወጡ ዘንድ እን​ዲሁ አደ​ረጉ፤ ነገር ግን አል​ቻ​ሉም፤ ቅማ​ሉም በሰ​ውና በእ​ን​ስሳ ላይ ነበረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ጠንቍዮችም በአስማታቸው ያወጡ ዘንድ እንዲሁ አደረጉ፤ ነገር ግን አልቻሉም፤ ቅማሉም በሰውና በእንስሳ ላይ ነበረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፀአት 8:18
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ፈርዖንም ጠቢባንንና አስማተኞችን ጠራ፤ የግብጽም አስማተኞች ደግሞ በአስማታቸው እንዲሁ አደረጉ።


ብጉንጅ በጠንቋዮቹና በግብጻውያን ሁሉ ላይ ነበር፤ ጠንቋዮቹም ብጉንጅ ስለ ነበረባቸው በሙሴ ፊት መቆም አልቻሉም፤


ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “ሰይጣንን እንደ መብረቅ ከሰማይ ሲወድቅ አየሁት።


አሁንስ ጥበበኞችህ የት አሉ? አሁን ይንገሩህ፤ የሠራዊት ጌታ በግብጽ ላይ ያሰበውን ይወቁ።


በነጋታውም ፈርዖን መንፈሱ ታወከበት፤ ስለዚህ በግብጽ አገር ያሉትን አስማተኞችና ጥበበኞች በሙሉ አስጠርቶ ሕልሞቹን ነገራቸው፥ ይሁን እንጂ ሕልሞቹን ሊተረጉምለት የቻለ አንድም ሰው አልተገኘም።


እያንዳንዳቸውም በትራቸውን ጣሉ፥ እባቦችም ሆኑ፤ የአሮን በትር ግን በትራቸውን ዋጠ።


እንቁራሪቶቹን ከአንተ ከቤቶችህም ከአገልጋዮችህም ከሕዝብህም ያርቃል፤ በዓባይ ወንዝ ብቻ ይቀራሉ።”


ማንም ወንድሙን አላየም፥ ሦስት ቀንም ሙሉ ማንም ከስፍራው አልተነሣም፤ የእስራኤል ልጆች ሁሉ ግን በተቀመጡበት ስፍራ ብርሃን ነበራቸው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች