ዘፀአት 8:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)16 ጌታም ሙሴን አለው፦ “ማልደህ ተነሣ፥ በፈርዖንም ፊት ቅረብ፤ እነሆ እርሱ ወደ ውኃ ይወርዳል፤ እንዲህም በለው፦ ‘ጌታ እንዲህ ይላል፦ እንዲያገለግለኝ ሕዝቤን ልቀቅ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም16 ከዚያም እግዚአብሔር ሙሴን፣ “አሮንን ‘በትርህን ሰንዝረህ የምድርን ትቢያ ምታ’ በለው፤ ከዚያም በግብጽ ምድር ያለው ትቢያ ሁሉ ተናካሽ ትንኝ ይሆናል” አለው። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም16 እግዚአብሔር ሙሴን “የምድሩን ትቢያ በበትሩ እንዲመታ ለአሮን ንገረው፤ በግብጽም አገር ሁሉ ትቢያው ወደ ተናካሽ ትንኝነት ይለወጣል” አለው። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)16 እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፥ “አሮንን፦ ‘በትርህን በእጅህ ዘርጋ፤ የምድሩንም ትቢያ ምታ’ በለው፤ ቅማልም በግብፅ ሀገር ሁሉ በሰውና በእንስሳ ላይ ይወጣል።” ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)16 እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፤ “አሮንን፦ ‘በትርህን ዘርጋ፤ በግብፅም አገር ሁሉ ቅማል እንዲሆን የምድሩን ትቢያ ምታ፤’ በለው።” ምዕራፉን ተመልከት |