ዘፀአት 8:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)13 እንዲሁም አደረጉ፤ አሮንም እጁን ዘረጋ፥ በበትሩም የምድሩን ትቢያ መታ፥ በሰውና በእንስሳም ላይ ተናካሽ ትንኝ ሆነ፤ በግብጽ ምድር ያለ የምድር ትቢያ ሁሉ ተናካሽ ትንኝ ሆነ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም13 እግዚአብሔር ሙሴ እንደ ለመነው አደረገ፤ ጓጕንቸሮቹም በየቤቱ ውስጥ፣ በየዐጥር ግቢውና በየሜዳው ሞቱ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም13 ሙሴ በጸለየውም መሠረት እግዚአብሔር በየቤቱ፥ በየቅጽር ግቢውና በየመስኩ ያሉት ጓጒንቸሮች ሁሉ ሞቱ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)13 እግዚአብሔርም ሙሴ እንደ አለ አደረገ፤ ጓጕንቸሮቹም ከቤት፥ ከመንደርም፥ ከሜዳም ሞቱ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)13 እግዚአብሔርም ሙሴ እንዳለ አደረገ፤ ጓጕንቸሮቹም ከቤት ከወጀድም ከሜዳም ሞቱ። ምዕራፉን ተመልከት |