Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘፀአት 8:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 እንደ ክምርም አድርገው ሰበሰቡአቸው፤ ምድሪቱም ገማች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ፈርዖንም፣ “ነገ ይሁን” አለው። ሙሴም እንዲህ ብሎ መለሰ፤ “እንደ አምላካችን እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም እንደሌለ ታውቅ ዘንድ አንተ እንዳልኸው ይሆናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ንጉሡም “እንግዲያውስ ነገውኑ ጸልይልኝ” አለ። ሙሴም እንዲህ አለ፤ “እንዳልከው አደርጋለሁ፤ አንተም እንደ አምላካችን እንደ እግዚአብሔር ያለ ሌላ አምላክ እንደሌለ በዚያን ጊዜ ታውቃለህ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ሙሴም፥ “ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቀር ሌላ አም​ላክ እን​ደ​ሌለ ታውቅ ዘንድ እሺ እንደ አልህ ይሁን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 እርሱም “ነገ” አለ። ሙሴም “አምላካችንን እግዚአብሔርን የሚመስል እንደሌለ ታውቅ ዘንድ እንደ ቃልህ ይሁን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፀአት 8:10
21 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ታላቅ ነህ! የሚመስልህ ማንም የለም፤ በጆሮአችን እንደሰማነው ሁሉ፥ ከአንተ በቀር አምላክ የለም።


አቤቱ፥ እንደ አንተ ያለ የለም፥ በጆሮአችንም እንደ ሰማን ሁሉ ከአንተ በቀር አምላክ የለም።


ይፈሩ ለዘለዓለሙም ይታወኩ፥ ይጐስቁሉ ይጥፉም።


አቤቱ፥ ከአማልክት የሚመስልህ የለም፥ ሥራህንም የሚመስል የለም።


አሕዛብ በሠሩት ጉድጓድ ወደቁ፥ በዚያችም በሸሸጓት ወጥመድ እግራቸው ተጠመደች።


ከአማልክት መካከል ጌታ ሆይ፥ እንደ አንተ ያለ ማን ነው? በቅድስና ባለግርማ፥ በምስጋና የተፈራህ፥ ድንቅንም የምታደርግ፥ እንደ አንተ ያለ ማን ነው?


ጌታም እንደ ሙሴ ቃል አደረገ፤ እንቁራሪቶቹም በየቤቶቹ፥ በየመንደሮቹና በሜዳም ሞቱ።


በዚህ ጊዜ መቅሠፍቴን ለልብህ በአገልጋዮችህ በሕዝብህም በምድር ሁሉ ላይ እልካለሁ ይህም እንደ እኔ ያለ እንደሌለ እንድታውቅ ነው።


ሙሴም እንዲህ አለው፦ “ከከተማ እንደ ወጣሁ እጄን ወደ ጌታ እዘረጋለሁ፤ ምድሪቱ የጌታ እንደ ሆነች እንድታውቅ፥ ነጎድጓዱ ይቆማል፥ በረዶውም ከእንግዲህ ወዲህ አይኖርም።


ቀኑ ምን እንደሚያመጣ አታውቅምና ነገ በሚሆነው አትመካ።


እንግዲህ እግዚአብሔርን በማን ትመስሉታላችሁ? ወይስ በምን ምሳሌ ታስተያዩታላችሁ?


እንግዲህ የሚስተካከለኝ ማን አለ? ከማንስ ጋር አመሳሰላችሁኝ? ይላል ቅዱሱ።


እኔ አምላክ ነኝና፥ ሌላም የለምና የቀድሞውን የጥንቱን ነገር አስቡ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ እንደ እኔም ያለ ማንም የለም።


‘ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ ታላቅነትህን የጸናችውንም እጅህን ለእኔ ለአገልጋይህ ማሳየት ጀምረሃል፥ በሰማይም ሆነ በምድርም እነዚህ ሥራዎችና ኃያል ተግባራት እንደ አንተ ማድረግ የሚችል አምላክ ማን ነው?


ጠላቶቻችን እንኳ እንደሚስማሙበት፥ ዓለታቸው እንደ እኛ ዓለት አይደለም።


“ይሹሩን ሆይ፥ በሰማያት ላይ ለረድኤትህ፥ በደመናትም ላይ በታላቅነት እንደሚሄድ እንደ ጌታ ያለ ማንም የለም።


ጌታም አምላካችሁ እንደሆነ እንድታውቁ ይህ ለእናንተ ተገልጧል፥ ከእርሱም ሌላ አምላክ የለም።


እንግዲህ፥ ጌታ በላይ በሰማይ በታችም በምድር አምላክ እንደሆነ፥ ሌላም እንደሌለ ዛሬ እወቁ፥ በልባችሁም ያዙት።


ነገ የሚሆነውን አታውቁም። ሕይወታችሁ ምንድነው? ለጥቂት ጊዜ ታይቶ ኋላ እንደሚጠፋ እንፋሎት አይደላችሁምን?


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች