Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘፀአት 7:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 አንተ ያዘዝሁህን ሁሉ ትነግረዋለህ፤ ወንድምህም አሮን የእስራኤልን ልጆች ከአገሩ እንዲለቅ ፈርዖንን ይነግረዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 እኔ የማዝህን ሁሉ ትናገራለህ፤ ወንድምህ አሮንም እስራኤላውያንን ከአገሩ እንዲወጡ ይለቅቃቸው ዘንድ ለፈርዖን ይነግረዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 እኔ የማዝህን ሁሉ ለአሮን ንገረው፤ እርሱም ከአገሩ እንዲወጡ እስራኤላውያንን ይለቅ ዘንድ ለንጉሡ ይነግረዋል፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 ያዘ​ዝ​ሁ​ህን ነገር ሁሉ አንተ ትነ​ግ​ረ​ዋ​ለህ፤ ወን​ድ​ም​ህም አሮን የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ከሀ​ገሩ ይለ​ቅቅ ዘንድ ለፈ​ር​ዖን ይን​ገ​ረው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 ያዘዝሁህን ነገር ሁሉ አንተ ትነግረዋለህ፤ ወንድምህም አሮን የእስራኤልን ልጆች ከአገሩ ይለቅቅ ዘንድ ከፈርዖን ጋር ይናገራል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፀአት 7:2
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሚክያስ ግን “ጌታ የሚገልጥልኝን ቃል ብቻ እንደምናገር በሕያው ጌታ ስም እምላለሁ!” ሲል መለሰለት።


አንተም ትናገረዋለህ ቃሎቹን በአፉ ታስቀምጣለህ፤ እኔም ከአፍህ ጋርና ከአፉ ጋር እሆናለሁ፥ የምታደርጉትንም አስተምራችኋለሁ።


እርሱ ለአንተ ብሎ ከሕዝቡ ጋር ይናገራል፤ እንዲህም ይሆናል፤ እርሱ አፍ ይሆንልሃል አንተም እንደ እግዚአብሔር ትሆንለታለህ።


ከዚህም በኋላ ሙሴና አሮን ሄደው ፈርዖንን እንዲህ አሉት፦ “የእስራኤል አምላክ ጌታ እንዲህ ይላል፦ ‘በምድረ በዳ በዓል እንዲያደርግልኝ ሕዝቤን ልቀቅ።’”


እርሱም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “እኔ ጌታ ነኝ፤ ለግብጽ ንጉሥ ለፈርዖን እኔ የምነግርህን ሁሉ ንገረው።”


ሙሴና አሮንም እንዲሁ አደረጉ፤ ጌታ እንዳዘዛቸው አደረጉ።


አንተ ግን ወገብህን ታጠቅ፥ ተነሥም፥ ያዘዝሁህንም ሁሉ ንገራቸው፤ በእነርሱ ፊት እንዳላስፈራህ አትፍራቸው።


ጌታ ግን እንዲህ አለኝ፦ “ ‘ብላቴና ነኝ’ አትበል፤ ወደ ምልክህ ሁሉ ትሄዳለህ፥ የማዝህንም ሁሉ ትናገራለህ።


እርሱም እንዲህ አለኝ፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ የምነግርህን ቃሌን ሁሉ በልብህ ያዝ፥ በጆሮህም ስማ።


የሰው ልጅ ሆይ፥ ለእስራኤል ቤት ጠባቂ አድርጌሃለሁ፥ የአፌን ቃል በሰማህ ጊዜ ታስጠነቅቅልኛለህ።


ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ አስተምሩአቸው፤ እነሆ እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።”


የእግዚአብሔርን ምክር ሁሉ ነግሬአችኋለሁና፤ ምንም አላስቀረሁባችሁም።


እኔ ያዘዝኋችሁን የጌታ አምላካችሁን ትእዛዝ ትጠብቃላችሁ እንጂ ባዘዝኋችሁ ቃል ላይ አትጨምሩም፥ ከእርሱም አታጎድሉም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች