Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘፀአት 7:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ጌታ እንዲህ ይላል፦ እኔ ጌታ እንደሆንሁ በዚህ ታውቃለህ፤ እነሆ እኔ በዓባይ ወንዝ ያለውን ውኃ በእጄ ባለው በትር እመታለሁ፥ ወደ ደምም ይለወጣል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፤ “እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ በዚህ ታውቃለህ፤ እይ! በዚህች በእጄ በያዝኋት በትር የአባይን ውሃ እመታለሁ፤ ወደ ደምም ይለወጣል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 አሁን ግን በሚያደርገው ነገር የእግዚአብሔርን ማንነት በግድ ታውቃለህ፤ እነሆ፥ እኔ በዚህ በትር የአባይን ወንዝ ውሃ እመታለሁ፤ ውሃውም ወደ ደም ይለወጣል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ በዚህ ታው​ቃ​ለህ፤ እነሆ፥ እኔ የወ​ን​ዙን ውኃ በእጄ ባለ​ችው በትር እመ​ታ​ለሁ፤ ውኃ​ውም ወደ ደም ይለ​ወ​ጣል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ በዚህ ታውቃለህ፤ እነሆ እኔ የወንዙን ውኃ በእጄ ባለችው በትር እመታለሁ፤ ውኃውም ተለውጦ ደም ይሆናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፀአት 7:17
30 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እንዲህም ይሆናል፤ እነዚህን ሁለት ምልክቶች ባያምኑ ቃልህንም ባይሰሙ፥ ከዓባይ ወንዝ ጥቂት ውኃን ውሰድ፥ በደረቅ መሬት ላይ አፍስሰው፤ ከዓባይ ወንዝ የወሰድከውም ውኃ በደረቁ መሬት ላይ ደም ይሆናል።”


ግብፃውያንም፥ እጄን በግብጽ ላይ ዘርግቼ የእስራኤልን ልጆች ከመካከላቸው ሳወጣ፥ እኔ ጌታ እንደሆንኩ ያውቃሉ።”


ፈርዖንም፦ “ቃሉን እንድሰማ እስራኤልንስ እንድለቅ ጌታ ማን ነው? ጌታን አላውቅም፥ እስራኤልንም ደግሞ አልለቅቅም” አለ።


እኔ ጌታ አምላካቸው እንደሆንሁ ያውቃሉ፥ በአሕዛብ እንዲማረኩ አድርጌአቸዋለሁና፥ ወደ ገዛ ምድራቸውም ሰብስቤአቸዋለሁና፥ ከእነርሱ አንድ ሰው እንኳ በዚያ አላስቀርም።


ታላቅ እሆናለሁ፥ እቀደሳለሁም፥ በብዙ አሕዛብ ዐይን የታወቅሁ እሆናለሁ፥ እኔ ጌታ እንደሆንሁ ያውቃሉ።


አሕዛብ በሠሩት ጉድጓድ ወደቁ፥ በዚያችም በሸሸጓት ወጥመድ እግራቸው ተጠመደች።


እነዚህ ትንቢት በሚናገሩበት ወራት ዝናብ እንዳይዘንብ ሰማይን የመዝጋት ሥልጣን አላቸው፤ ውሃዎችንም ወደ ደም ለመለወጥ በሚፈልጉበትም ጊዜ ሁሉ በመቅሠፍት ምድርን የመምታት ሥልጣን አላቸው።


ሁለተኛውም መልአክ መለከቱን ነፋ፤ በእሳት የሚቃጠል ታላቅ ተራራን የሚመስል ነገር በባሕር ተጣለ፤ የባሕርም ሲሶው ደም ሆነ፤


የግብጽንም ምድር ወና እና ባድማ ባደረግሁ ጊዜ፥ ሞላዋንም ያጣች ምድር ባደረግኋት ጊዜ፥ የሚኖሩባትንም ሁሉ በመታሁ ጊዜ፥ እኔ ጌታ እንደሆንኩ ያውቃሉ።


እንግዲህ በግብጽ ላይ ፍርድን አመጣለሁ፤ እኔም ጌታ እንደሆንሁ ያውቃሉ።


እሳትን በግብጽ ሳነድድ፥ ረዳቶችዋም ሁሉ ሲሰበሩ፥ እኔ ጌታ እንደሆንሁ ያውቃሉ።


የግብጽ ምድር ባድማና ውድማ ትሆናለች፥ እኔም ጌታ እንደሆንሁ ያውቃሉ፤ ምክንያቱም ወንዙ የእኔ ነው፥ የሠራሁትም እኔ ነኝ ብሏልና።


ውኃቸውን ወደ ደም ለወጠ፥ ዓሦቻቸውንም ገደለ።


ይፈሩ ለዘለዓለሙም ይታወኩ፥ ይጐስቁሉ ይጥፉም።


ወንዞቻቸውንም ወደ ደም ለወጠ፥ ምንጮቻቸውን እንዳይጠጡ።


እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፥ አንተ ብቻ አምላክ መሆንህን የዓለም መንግሥታት ሁሉ ያውቁ ዘንድ አሁን ከአሦር ንጉሥ በመታደግ አድነን።”


አንድ የእግዚአብሔር ሰው ወደ ንጉሥ አክዓብ ቀርቦ “ጌታ የተናገረው ቃል ይህ ነው፦ ‘ሶርያውያን ጌታ የኮረብቶች አምላክ እንጂ የሜዳዎች አምላክ አይደለም’ ብለዋል፤ ከዚህም የተነሣ እኔ እጅግ ብዙ በሆነው ሠራዊታቸው ላይ ድልን አቀዳጅሃለሁ፤ አንተና ሕዝብህም እኔ ጌታ መሆኔን ታውቃላችሁ” አለው።


ለእኔ ሕዝብ አድርጌ እቀበላችኋለሁ፥ አምላክም እሆናችኋለሁ፤ እኔም ከግብጽ ጭቆና ያወጣኋችሁ ጌታ አምላካችሁ እንደሆንሁ ታውቃላችሁ።


ፈርዖንም፦ “የሚወለደውን ወንድ ልጅ ሁሉ ወደ ዓባይ ወንዝ ጣሉት፥ ሴትን ልጅ ሁሉ ግን በሕይወት እንድትኖር ተዉአት” ብሎ ሕዝቡን ሁሉ አዘዘ።


ሙሴና አሮንም ልክ ጌታ እንዳዘዛቸው እንዲሁ አደረጉ፤ በትሩንም አነሣ፥ በፈርዖንና በአገልጋዮቹም ፊት በዓባይ ወንዝ የነበረውን ውኃ መታ፤ በዓባይ ወንዝ ላይ የነበረው ውኃ ሁሉ ወደ ደም ተቀየረ።


ይህም በልጅህና በልጅ ልጅህ ጆሮ እንድትነግርና ግብፃውያንን እንዴት እንዳሞኘኋቸው፥ በመካከላቸው ያስቀመጥኩት ምልክቶቼም ጌታ እንደሆንኩ እንድታውቁ ነው።”


ቁጣ ከተሞላበት ቅጣት ጋር ታላቅ በቀል አደርግባቸዋለሁ፥ በቀሌን በእነሱ ላይ ባደረግሁ ጊዜ፥ እኔ ጌታ እንደሆንሁ ያውቃሉ።


የምትዋኝባትን ምድር እስከ ተራሮች ድረስ በደምህ አጠጣለሁ፥ መስኖዎች ከአንተ ይሞላሉ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች