ዘፀአት 5:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)16 ለአገልጋዮችህ ገለባ አልተሰጠም፥ ጡብ ሥሩ ይሉናል፤ እነሆ አገልጋዮችህ ተገረፍን፤ ይህም ሕዝብህን ሐጢአተኛ ያደርጋል።” ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም16 ለእኛ ለባሮችህ ጭድ ሳያቀርቡልን ሸክላ ሥሩ ይሉናል፤ ጥፋቱ የገዛ ሰዎችህ ሆኖ ሳለ እኛ ባሮችህ ግን እንገረፋለን።” ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም16 ምንም ገለባ ሳይሰጠን ጡብ እንድንሠራ ታዘናል፤ ከዚህም ጋር እነሆ፥ እየተገረፍን ነው፤ ስሕተቱ ግን የገዛ ሕዝብህ ነው እንጂ የእኛ አይደለም” ሲሉ አቤቱታቸውን አቀረቡ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)16 እነሆም፥ አገልጋዮችህ ይገረፋሉ፤ ይገፋሉም፤ ግፉም በአንተ ሕዝብ ላይ ነው” ብለው ጮኹ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)16 ገለባ አይሰጡንም፤ የጡቡንም ሥራ እንድንሠራ ያዝዙናል፤ እነሆም ባሪያዎችህን ይገርፉናል፤ ግድፈቱ ግን በአንተ ሕዝብ ላይ ነው” ብለው ጮሁ። ምዕራፉን ተመልከት |