ዘፀአት 40:38 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)38 በጉዞአቸው ሁሉ በእስራኤል ቤት ሁሉ ፊት የጌታ ደመና በቀን በማደሪያው ላይ፥ በሌሊትም እሳት በዚያ ላይ ነበረ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም38 ስለዚህ በጕዟቸው ሁሉ ወቅት፣ በእስራኤል ቤት ፊት ሁሉ የእግዚአብሔር ደመና በቀን ከማደሪያው በላይ፣ በሌሊትም እሳቱ በደመናው ውስጥ ነበር። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም38 በሚጓዙበት ጊዜ ሁሉ በቀን የእግዚአብሔርን ክብር የሚገልጠው ደመና ድንኳኑን ሲሸፍን፥ በሌሊት ደግሞ በደመናው ውስጥ እሳት ያዩ ነበር። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)38 ደመና በቀን በድንኳኑ ላይ ነበርና፥ እሳቱም በሚጓዙበት ሁሉ በሌሊት በእስራኤል ሁሉ ፊት በእርስዋ ላይ ነበርና። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)38 በመንገዳቸውም ሁሉ በእስራኤል ቤት ሁሉ ፊት የእግዚአብሔር ደመና በማደሪያው ላይ በቀን ነበረና፥ እሳትም በሌሊት በዚያ ላይ ነበረና። ምዕራፉን ተመልከት |