ዘፀአት 4:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)7 እርሱም፦ “እጅህን ወደ ብብትህ መልስ” አለው። እጁንም ወደ ብብቱ መለሰው፥ ከብብቱም ባወጣው ጊዜ ተመልሶ ገላውን እንደሚመስል አየ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም7 “አሁንም ደግሞ እጅህን ወደ ብብትህ መልሰህ አስገባ” አለው። ሙሴም እጁን መልሶ ብብቱ ውስጥ አስገባ፤ እንደ ገና እጁን ከብብቱ ውስጥ ባወጣት ጊዜ፣ ተመልሳ እንደ ሌላው የሰውነቱ ክፍል ሆነች። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም7 እግዚአብሔርም “እጅህን እንደገና ወደ ብብትህ አስገባ” አለው። ሙሴም እጁን ወደ ብብቱ አስገባ፤ መልሶም ባወጣው ጊዜ ተመልሶ እነሆ፥ እንደ ሌላው ሰውነቱ ጤናማ ሆነ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)7 ዳግመኛም፥ “እጅህን ወደ ብብትህ መልስ” አለው። እጁንም ወደ ብብቱ መለሳት፤ “እጅህን ከብብትህ አውጣ” አለው፤ እጁንም ከብብቱ አወጣ፤ ተመልሳም ገላውን መሰለች። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)7 እርሱም፦ እጅህን ወደ ብብትህ መልስ አለው። እጁንም ወደ ብብቱ መለሳት፥ ከብብቱም ባወጣት ጊዜ እነሆ ተመልሳ ገላውን መሰለች። ምዕራፉን ተመልከት |