ዘፀአት 4:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)18 ሙሴም ሄደ፥ ወደ አማቱ ወደ ይትሮ ተመለሰ፥ እርሱም፦ “እባክህን በግብጽ ወዳሉ ዘመዶቼ እንድመለስ እስካሁንም በሕይወት እንዳሉ ሄጄ እንዳይ ፍቀድልኝ” አለው። ይትሮም ሙሴን፦ “በሰላም ሂድ” አለው። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም18 ሙሴም ወደ ዐማቱ ወደ ዮቶር ተመልሶ ሄደና፣ “ወገኖቼ እስካሁን በሕይወት መኖራቸውን አይ ዘንድ ወደ ግብጽ ተመልሼ እንድሄድ እባክህ ፍቀድልኝ” አለው። ዮቶርም፣ “ሂድ፤ በሰላም ያግባህ” አለው። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም18 ሙሴም ወደ ዐማቱ ወደ የትሮ ተመልሶ ሄደና “በግብጽ ወደሚኖሩት ወገኖቼ ተመልሼ ሄጄ በሕይወት መኖራቸውን እንዳይ ፍቀድልኝ” አለው። የትሮም ፈቅዶ “በሰላም ሂድ” አለው። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)18 ሙሴም ሄደ፤ ወደ አማቱ ወደ ዮቶርም ተመለሰ፥ “እስከ ዛሬ በሕይወት እንደ አሉ አይ ዘንድ ተመልሼ ወደ ግብፅ ወደ ወንድሞች እሄዳለሁ” አለው። ዮቶርም ሙሴን፥ “በደኅና ሂድ” አለው። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)18 ሙሴም ሄደ፤ ወደ አማቱ ወደ ዮቶር ተመለሰ፤ “እስከ ዛሬ በሕይወት እንዳሉ አይ ዘንድ ተመልሼ ወደ ግብፅ ወደ ወንድሞቼ ልሂድ፤” አለው። ዮቶርም ሙሴን፦ “በሰላም ሂድ” አለው። ምዕራፉን ተመልከት |