Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘፀአት 39:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 በመቅደሱ ለማገልገል ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊና ከቀይ ግምጃ በብልሃት የተሠራ ልብስ አደረጉ፥ ጌታም ሙሴን ባዘዘው መሠረት ለአሮን የተቀደሱ ልብሶችን ሠሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ለመቅደሱ አገልግሎት ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊና ከቀይ ማግ የተፈተሉ ልብሶችን ሠሩ፤ እንዲሁም እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው ለአሮን የተቀደሱ ልብሶችን ሠሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ካህናቱ በተቀደሰው ስፍራ ሲያገለግሉ የሚለብሱአቸውን እጅግ የተዋቡትን የካህናት ልብሶች ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊና ከቀይ ከፈይ ሠሩ፤ የአሮንንም የክህነት ልብሶች እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ሠሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 የቀ​ረ​ውም የመባ ወርቅ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ይሠ​ሩ​በት ዘንድ ንዋየ ቅድ​ሳት ሆኖ ተሠራ። ከሰ​ማ​ያዊ፥ ከሐ​ም​ራ​ዊም ከቀይ ግም​ጃም ለመ​ቅ​ደሱ አገ​ል​ግ​ሎት ልብ​ሶ​ችን ሠሩ፤ እን​ዲ​ሁም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው ለአ​ሮን የተ​ቀ​ደ​ሰ​ውን ልብስ ሠሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘው፥ በመቅደሱ ለማገልገል ከሰማያዊ ከሐምራዊም ከቀይ ግምጃም በብልሃት የተሠራ ልብስ፥ ለአሮንም የተቀደሰውን ልብስ አደረጉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፀአት 39:1
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ምስክርነትህ እጅግ የታመነ ነው፥ አቤቱ፥ ለረጅም ዘመን፥ ለቤትህ ቅድስና ይገባል።


ሰማያዊ፥ ሐምራዊ፥ ቀይ ግምጃ፥ ጥሩ በፍታና የፍየል ጠጉር፥


“ከተፈተለ ከጥሩ በፍታ፥ ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊና ከቀይ ግምጃ የተሠሩ ዐሥር መጋረጆች ያሉበትን ድንኳን ሥራ፤ ብልህ ሠራተኛ እንደሚሠራ ኪሩቤል በእነርሱ ላይ ይሁኑ።


ወርቅ፥ ሰማያዊ፥ ሐምራዊ፥ ቀይም ግምጃና ጥሩ በፍታም ይውሰዱ።


በብልሃት የተሠራውን ልብስ፥ በክህነት እኔን የሚያገለግሉበትን የካህኑ የአሮን የተቀደሱ ልብሶች የልጆቹ ልብሶች፥


በመቅደስ ውስጥ ለማገልገል በብልሃት የተሠሩትን ልብሶች፥ በክህነት እንዲያገለግሉበት የተቀደሱትን የካህኑን የአሮን ልብሶችና የልጆቹን ልብሶች።”


ሰማያዊ፥ ሐምራዊ፥ ቀይ ግምጃ፥ ጥሩ በፍታ፥ የፍየል ጠጉር፥ ቀይ የአውራ በግ ቁርበት፥ የአቆስጣ ቁርበት ያላቸው ሰዎች ሁሉ አመጡ።


በአደባባዩ ዙሪያ ያሉትን እግሮች፥ የአደባባዩን መግቢያ እግሮች፥ የማደሪያውን ካስማዎች ሁሉና በአደባባዩ ዙሪያ ያሉትን ካስማዎች ሁሉ ሠራ።


በመቅደስ ውስጥ ለማገልገል በብልሃት የተሠሩትን ልብሶች፥ በክህነትም እንዲያገለግሉበት የተቀደሱትን የካህኑን የአሮንን ልብሶችና የልጆቹን ልብሶች አመጡ።


ካህናቱም ከገቡ በኋላ የሚያገለግሉበትን ልብስ ሳያወልቁ ከመቅደሱ ወደ ውጭው አደባባይ አይወጡም፥ የተቀደሱ ናቸውና፤ ወደ ሕዝቡ ቦታ ሲቀርቡ ሌላ ልብስ መልበስ አለባቸው።


የቤቱ ሕግ ይህ ነው፤ በተራራው ራስ ላይ በዙሪያው ያለው ስፍራ ሁሉ የተቀደስ ይሆናል። እነሆ፥ የቤቱ ሕግ ይህ ነው።


የዘለዓምን ቤዛነት አግኝቶ፥ አንድ ጊዜ ፈጽሞ ወደ ቅድስት በገዛ ደሙ ገባ እንጂ፥ በፍየሎችና በጥጆች ደም አይደለም።


ሊቀ ካህናትም በየዓመቱ የሌላውን ደም ይዞ ወደ ቅድስት ደጋግሞ እንደሚገባ፥ ራሱን ብዙ ጊዜ ሊያቀርብ አልገባም፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች