Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘፀአት 38:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 የአደባባዩ መግቢያ መጋረጃ ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊ፥ ከቀይ ግምጃና ከጥሩ በፍታ የተጠለፈ ነበረ፤ ርዝመቱ ሀያ ክንድ፥ ቁመቱ እንደ አደባባዩ መጋረጃዎች አምስት ክንድ ነበረ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 በአደባባዩ መግቢያ ላይ ያለው መጋረጃ ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ማግና የጥልፍ ባለሙያ ከጠለፈው፣ በቀጭኑ ከተፈተለ በፍታ የተሠራ ነበር፤ ቁመቱ ሃያ ክንድ፣ እንደ አደባባዩ መጋረጃዎች ከፍታው ዐምስት ክንድ ነበረ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ወደ ድንኳኑ የሚያስገባው ደጃፍ መጋረጃ ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊና ከቀይ በፍታ ተፈትሎ በእጅ ጥበብ ካጌጠ ቀጭን ሐር የተሠራ ነበር፤ እርሱም እንደ ድንኳኑ በር መግቢያ መጋረጃዎች ሁሉ ርዝመቱ ዘጠኝ ሜትር ቁመቱም ሁለት ሜትር ነበር፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 የአ​ደ​ባ​ባ​ዩም ደጅ መጋ​ረጃ ከሰ​ማ​ያዊ፥ ከሐ​ም​ራ​ዊም፥ ከቀ​ይም ግምጃ ፥ ከጥ​ሩም በፍታ በጥ​ልፍ አሠ​ራር የተ​ሠራ ነበረ፤ ርዝ​መቱ ሃያ ክንድ ነበረ፤ ቁመ​ቱም እንደ አደ​ባ​ባዩ መጋ​ረ​ጃ​ዎች አም​ስት ክንድ ነበረ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 የአደባባዩም ደጅ መጋረጃ ከሰማያዊ ከሐምራዊም ከቀይም ግምጃ፥ ከጥሩም በፍታ በጥልፍ አሠራር የተሠራ ነበረ፤ ርዝመቱ ሀያ ክንድ ነበረ፥ ቁመቱም እንደ አደባባዩ መጋረጆች አምስት ክንድ ነበረ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፀአት 38:18
5 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሰሎሞንም ከሰማያዊው ከሐምራዊውም ከቀዩም ሐር ከጥሩም በፍታ መጋረጃውን ሠራ፥ ኪሩቤልንም ጠለፈበት።


“ከተፈተለ ከጥሩ በፍታ፥ ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊና ከቀይ ግምጃ የተሠሩ ዐሥር መጋረጆች ያሉበትን ድንኳን ሥራ፤ ብልህ ሠራተኛ እንደሚሠራ ኪሩቤል በእነርሱ ላይ ይሁኑ።


ለድንኳኑም ደጃፍ ከሰማያዊ ከሐምራዊም ከቀይም ግምጃ ከተፈተለ ከጥሩ በፍታም በጥልፍ አሠራር የተሠራ መጋረጃ አድርግለት።


የምሰሶዎቹ እግሮች ከነሐስ የተሠሩ፥ የምሰሶዎቹ ኩላቦችና ዘንጎች ከብር የተሠሩ ነበሩ፤ የምሰሶዎቹ ጉልላቶች በብር ተለብጠው ነበር፤ በአደባባዩ ያሉ ምሰሶዎች ሁሉ የብር ዘንጎች ነበሩአቸው።


ምሰሶዎቹ አራት ነበሩ፤ ከነሐስ የተሠሩ እግሮች አራት፥ ኩላቦቹ ከብር የተሠሩ ነበሩ፥ ጉልላቶቻቸውና ዘንጎቻቸው በብር ተለብጠው ነበር።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች